የሼፕ ኢትዮጵያ አጋር ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፣ የስራ ባልደረቦቻቸው እና ስፖንሰሮች የሻንቶ ማህበረሰብ  ቤተ መፃህፍቱን ጉብኝት አድርጓል።

የሻንቶ(ዎላይታ) ማህበረሰብ ቤተመፃህፍት በክልሉ ውስጥ ካሉት ግዙፍ የማህበረሰብ ቤተ-መጻሕፍት አንዱ ሲሆን ላይብሬሪው  ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ለምርምር እና ጥናት አገልግሎት የሚውሉ ከ22,000 በላይ በሀገር ውስጥ የማይገኙ ውድ መጽሐፍትን መያዙ ተገልጿል።

በተጨማሪም በእያንዳንዱ ላይ ከ 20,000 በላይ መጽሐፍት የተጫኑባቸው 20  ኮምፒውተሮች የሚገኝበትና ወደፊት ቤተ መፃህፍቱን ወደ ዲጂታል ላይብሬሪ ደረጃ ለማሳደግ መታቀዱንም ድርጅቱ አስታውቋል።

በሐምሌ 2022፣ የህጻናት ንባብ ክፍልን ከአዋቂዎች ንባብ ክፍል ለመለየት ቤተ መፃህፍቱ በሁለት ክፍሎች ተከፍሎ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል።

ነገር ግን፣ ቤተ መፃህፍቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ የውሃ፣ መደርደሪያና የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶች ያላሟላ በመሆኑ የቤተ መፃህፍቱ ቀሪ ስራዎች እንዲጠናቀቁ የሚመለከታቸው አካላት ለውጤታማነቱ የበኩላቸው እንዲያበረክቱ ሼፕ ኢትዮጵያ ጥሪውን አቅርቧል።

ከአንድ ሳምንት በፊት ከሼፕ ኢትዮጵያ አጋር ድርጅቶች አንዱ የሆነው “የፓርትነርስ ዊዝ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፣ የስራ ባልደረቦቻቸው እና ስፖንሰሮች ቤተ መፃህፍቱን ጉብኝት ማድረጋቸውም ተገልጿል።

ሼፕ ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት በእንጂነር ደሳለኝ ዳካ የተቋቋመ ሲሆን በሻንቶ ከተማ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ካስገነባው ቤተመጻሕፍት በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ አለምአቀፍ በጎ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በርካታ ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ተማሪዎችን ሙሉ ወጪ በመሸፈን ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩንቨርስቲ በማስተማር፣ ባሎቻቸውን በሞት ያጡ ወገኖቹን በተለያዩ መንገዶች ቋሚ ድጋፍ እንዲገኙ በማድረግ እንዲሁም በትምህርትና በጤና ዘርፍ በዎላይታ ዞን፣ በጋሞ ዞን እንዲሁም በሲዳማ ክልል እየሰራ የሚገኝ ሀገር በቀል ድርጅት ስለመሆኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *