

በዎላይታ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገርአቀፍ ደረጃ ፓለቲካ ፓርቲነት ለመንቀሳቀስ የሚያስችል የመስራች ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ያካሄደው የዎላይታ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ምን አላማ ይዞ ተነሳ❓ እንዴት፣ በምን፣ ለማንና ማን ማን የተሳተፉበት ፓርቲ ነው ነው❓
👉 ፓርቲው እውቅ የብሄሩ ተወላጅ ሳይንትስቶች፣ ተመራማሪዎች፣ ዶክተሮች፣ በሁሉም ዘርፍ ተሰማርቶ ሀገር ውስጥ ወጭ ሀገር የሚኖሩ የመብት ተሟጋች ሀሳብ አመንጭነትና ድጋፍ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ በአመራርነት በሰሩ እና አባል በነበሩ ግለሰቦች አስተባባሪነት እየተመሰረተ የሚገኝ ተስፋ የተጣለበት ሀገራዊ ፓለቲካ ፓርቲ ነው፥
👉የዎላይታ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ዎህነን) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ያገኘው ከአራት ወራት ገደማ በፊት ነበር፥
👉ዎህነን ጊዜያዊ ፈቃዱን ካገኘ በኋላ ሀገራዊ ፓርቲ ሆኖ ለመመዝገብ በአምስት ክልሎች እና በአንድ የከተማ አስተዳደር የመስራች አባላትን ፊርማ ሲያሰባስብ ቆይቷል፥
👉 ፓርቲው በትግራይ፣ አፋር ፣ ኦሮሚያ፣ ቀድሞ ደቡብ/ብ/ሕ/ክልል፣ ጋምቤላ ክልሎች እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 13 ሺህ ገደማ ፊርማ አሰባስቧል፥
👉 የንቅናቄው ዋና አላማ በጠንካራ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እና በዎላይታዊ ማንነቱ የማይደራደረው የዎላይታ ሕዝብ ከ70 በመቶ የሚልቀዉ አሁን ዎላይታ ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ውጪ የሚኖረዉ የህዳጣን (በሌሎች አከባቢ የሚኖሩ) መብት እንዲከበርለት በትኩረት ይሰራል፥
👉በሀገሪቱ በተለይም በአከባቢው ያለው ህዝብ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እንዲሁም ፓለቲካዊ መብቶች እንዲጠበቁ በግለሰብ ደረጃ ከመንቀሳቀስ ይልቅ በተደራጀ ሁኔታ ለመስራት እንዲያስችል የተደራጀ ነው፥
👉በአከባቢው ተፎካካሪ ፓለቲካ ፓርቲዎች ላይ የተለያዩ ጫናዎች በገዢው ፓርቲ የሚደርስ ቢሆንም ይሄንን ጫና ተቋቁሞ ለህዝብ ነፃነትና በሀገሪቱ በሁሉም ዘርፍ እኩል ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በሙሉ አቅም በውጭ ሀገርና ሀገርውስጥ የሚገኙ ለህዝብና ለለውጥ ተቆርቋሪ የሆኑ ግለሰቦች ጥምረት ይንቀሳቀሳል፥
👉 በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖሩ የዎላይታ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ይገኛል ያለውን “ማንነት ተኮር ጥቃት ማስቆም” ከቀዳሚ አጀንዳዎቹ አንዱ ሲሆን የዎላይታ የክልልነት ጥያቄን ምላሽ እንዲያገኝ ይደግፋል፥
👉 የዎላይታ ህዝብ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ “ተበትኖ” የሚኖር በመሆኑ የሚቋቋመው የፖለቲካ ፓርቲ “ሀገር አቀፍ” እንዲሆን ተደርጓል፥
👉 ዎህነን ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሰረት መስራች አባላት ውስጥ 40 በመቶው የአንድ ክልል መደበኛ ነዋሪ መሆን እንዳለባቸው በተደነገገው አዋጁ፤ ቀሪዎቹ ቢያንስ በሌሎች አራት ክልሎች ውስጥ መደበኛ ነዋሪ መሆን አለበት በሚለው ህግ የተቋቋመ ፓርቲ ነው፥
👉 ሀገራዊ ፓርቲ ለመሆን አስቀድሞ በአምስት ክልሎች እና በአዲስ አበባ ከተማ እስካሁን ድረስ 30 ሺህ ገደማ እጩ አባላት ተመዝግቧል፥
👉 የዎላይታ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ፓርቲ ማቋቋም ካስፈለገባቸው ገፊ ምክንያቶች ውስጥ፤ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚኖረው የዎላይታ ህዝብ ላይ “በተደጋጋሚ የሚደርሰው ማንነት ተኮር ጥቃት” አንዱ ነው፥
👉 በሀገሪቱ በዎላይታ ህዝብና ሌሎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት “በኢትዮጵያዊ ሆደ ሰፊነት” የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ ፓርቲው እንዲወለድ ምክንያቶች ናቸው፥
👉 ዎህነን በፕሮግራሙ ካካተታቸው ጉዳዮች ውስጥ የክልልነት ጥያቄ አንዱ ነው፥
👉 ፓርቲው በ“እውነተኛ ህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም ያምናል፥
👉 የዎላይታ ህዝብ በዚህ ስርዓት ውስጥ ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት፤ ሌላኛው የፓርቲ ዓላማ ነው፥
👉ህዝቡ በፌደራሊዝም ስርዓቱ ከሚጠቅምባቸው ጉዳዩች ውስጥ፤ ዎላይትኛ የፌደራል የስራ ቋንቋ መደረጉ አንዱ ሲሆን “መንግስት በሚያግባባ ቋንቋ ሰፊውን የገጠሩን ማህበረሰብ በማንቀሳቀስ ለልማት መጠቀም የሚያስችል መሰረት እንዲኖረው ይሰራል፥
👉ዎህነን በዎላይታ ፓለቲካ ፓርቲ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራዊ ፓርቲነት ለመንቀሳቀስ የሚመዘገብ ነው፥
👉የዎላይታ ህዝብ ለዘመናት የራሱ የሆነ አማራጭ ሀገራዊ ፓርቲ ባለመኖሩ እውነተኛ ተወካይ ባለማግኘቱ የተፈጠረውን ከፍተኛ ጉዳት በፓርላማ ሀቀኛ ተወካይ እንዲወክል አበክሮ ይሰራል፥
👉የመስራች ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ዕለት (14/08/2015 ዓ.ም) በዎላይታ ጉተራ አዳራሽ ከስድስቱም ነባር ክልሎች የመስራች ጠቅላላ ጉባኤ አባላት፣ የምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች፣ የክብር እንግዶች እንዲሁም የተለያዩ ሚዲያዎች በተገኙበት ተካሂዷል፥
👉በመስራች ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲው ዓላማዎቹ በዝርዝር የተካተቱበትን የመመስረቻ ጽሁፍ፣ ፕሮግራም እና ህገ ደንብ ለውይይት ከቀርበ በኃላ ተተችተው የፀደቀ ሲሆን የፓርቲው ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ዋና ፀሃፊ ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ምርጫም በዛሬው ዕለት በሰላም ተከናወነው ተጠናቋል፥
👉በተጨማሪም ንቅናቄው ሁሉአቀፍ ተሳትፎ በማረጋገጥ እውነተኛ ለውጥ እንዲመጣ ሌሎች ፓርቲ አጋሮች በጋራ ለመንቀሳቀስ እንዲመጡ በተሻለ አደራጃጀት ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ነው፥
👉ጠንካራ ህብረብሔራዊ ፌደራላዊ ሥርዓት ለጠንካራ ሀገር ግንባታ” መሪ ቃሉ አድርጎ የተነሳው የዎላይታ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ፓርቲ በሀገራዊ ፓርቲነት ለመንቀሳቀስ ለመጀመሪያ ጊዜ የመስራች ጉባኤ ያካሄደ ሲሆን ዎላይታን መነሻ ያደረጉ ዎብን እና ዎህዴግ ክልል አቀፍ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉ ፓርቲ ናቸው።




