በምስራቅ አፍርካ በአይነቱ ለየት ያለ በዎላይታ በበሎሶ ቦምቤ ወረዳ አጆራ ቀበሌ የሚገኝ ውብ “አጆራ” መንትያ ፏፏቴዎች፤ ከረጅም ርቀት ወደ ምድር የሚንደረደሩ ናቸው።

ሁለቱ ፏፏቴዎች የተመሰረቱት ሶኬ እና አጃንቾ ተብለው በሚጠሩ ወንዞች ነው፣ ሶኬ ወንዝ በሰሜን፣ አጀንቾ ደግሞ በስተደቡብ በኩል ይገኛሉ፡፡

ስያሜያቸው ከሚንደረደሩበት ትልቅ ገደል ውሰጥ ለዘመናት ይኖሩ ከነበረው “አጆራ” ወይም “ያጋ” የተባሉ ዎላይታ ጎሳዎች ነው የሚሉ አሉ፡፡

እየሮጡ የሚዘምሩ፤ ቁልቁለቱን ሲንደረደሩ የማያዳፋቸው፡፡

ሲጤሱ የኖሩ ውብ ሁለት ሆነው አንድ ውበት አንድ መልክ አንድ መደመም መፍጠር የቻሉ ጸጋዎች ናቸው፡፡

የሶኬ ፏፏቴ 170 ሜትር ገዳማ ከሰማይ ወደ ጥልቁ ይወርዳል፡፡

አጃንቾ ከሶኬ የበለጠ ተንደርዳሪ ነው፡፡

210 ሜትር ቁልቁል ይወርዳል፡፡

በሁለቱ ፏፏቴዎች መሀከል ያለው ርቀት በቀጥታ መስመር ሲለካ 650 ሜትር (2133 ጫማ) እንደሚሆን ይገመታል፡፡

ወርደው ምድር ሲነኩ የተለየ ድምጽ ያሰማሉ፡፡

ገና ምድሩን ሳይነኩት የሚተፉት ጭስ በተለይም በክረምት ናፍጣ የበዛበት መኪና፣ በበጋ ደግሞ ጉም የሚንደባለልበት ሰማይ ያስመስላቸዋል፡፡

አካባቢው አረንጓዴ ነው፡፡

የተለያየ ብዝሃ ህይወት መኖሪያ መሆን ችሏል፡፡

ወንዞቹም ከፏፏቴዎቹ አለፍ ብለው ውህደት ይፈጥሩና፣ ለተጨማሪ 10 ኪ.ሜ (6 ማይል) ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በማምራት ከኦሞ (ጊቤ) ወንዝ ይቀላቀላሉ።

በምስራቅ አፍርካ በአይነቱ ለየት ያለው አጆራ መንትያ ፏፏቴ ሁለት ወንዞች ውጤት ሲሆን ሶኬና አጃንቾ ይባላሉ።

የሶኬ ፏፏቴ 170 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን የአጃንቾ ፏፏቴ 210 ሜትር ከፍታ አለው፡፡

ሁለቱ ወንዞች ተገናኝቶ አንድ ትልቅ ሌላ ተጨማሪ ፏፏቴ የሚፈጥር ሲሆን ስያመውም ቡቡቃ ይባላላ፡፡ አጠገቡ ለሚደርስ ሰው የሚያሰማው ድምጽ እጅግ ይማሪካል፤ ነፍስና ስጋን ይማሪካል፡፡

ቦታውን የተለያዩ የቀድሞ ሀገር መሪዎች በተለይም አጼ ኃይሌስላሰ፣ ኮሌኔል መንግስቱ ኃይሌማሪያም አቶ ኃይሌማሪያም ደሳለኝ፣ አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስና ሌሎች የሀገራችን ታዋቂ ግለሰቦች በተለያዩ ጊዜያት ደጋግመው ጉብኝት ማድረጋቸውን ከተለያዩ መረጃ ምንጮች ለመረዳት ችለናል፡፡

ፏፏቴው አጠገብ እጅግ የሚገርም ዋሻና ከተራራው የሚወረወሩ ምንጮች ትንፋሽ ቀጥ ያደርጋሉ፡፡

ይህ በኢትዮጵያ ትልቅ የቱሪስት መዳረሻ በመሆን አከባቢውን ከማስተዋወቅ ባለፈ ለተለያዩ አካላት ስራ ዕድል ተፈጥሮ ገቢ ምንጭ በመሆን የውጭ ምንዛሪ ሊያሰገኝ የሚችል የቱሪስት መስህብ ከግንዛቤ ማነስና ትኩረት ከመነፈጉ የተነሳ እጅግ አስቸጋሪ ሁነታ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ባለሀብቶች ይህን ቦታ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን በአከባቢው የተለያዩ መሰረተ ልማት እንዲሰራ የበኩላቸውን ቢወጡ መልካም ነው እንላለን።

Ajjora Falls-The only East #African twin falls, Its the most spectacular waterfall with the most stunning view one can ever come across. As everything looks more exquisite when soaked in the rain, planning to visit some places is not a bad idea.

During the rainy season, the water level of the fall rises and the surroundings turn even more green which adds up to its charm.

Landoforigins #VisitEthiopia #Ethiopianrainyseason #Ajjorafalls #Wintertravel #Wolaita #waterfalls #ethiopia #vacation#eastafrica

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *