Wolaita Sodo Water

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ሶዶ ከተማ በዩንቨርስቲው መንገድ አከባቢ በዛሬው ዕለት ከፍተኛ ግፊት ያለው የውሃ መስመር ተፈንዶ ውሃ በከፍተኛ ኃይል ወደ ላይ ሲረጭ የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል በ WT Media ታይቷል። 

በምስሉ ላይ እንደሚስተዋለው፤ በመንገድ ዳር አካባቢ በተፈጠረው የውሃ ፍንዳታ ሳቢያ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የባጃጅ፣ የሞተር ሳይክል እና የመኪና ተሽከርካሪዎች እንዲሁም እግረኞች አልፈው ሲያልፉ ይታያሉ፤ በስፍራውም የጸጥታ አካላትን ጨምሮ የተወሰኑ ሰዎች ተሰብስበው ሁኔታውን ሲከታተሉ ተስተውሏል።

በቪዲዮው ላይ ከተሰማው የውሃ ፍንዳታ ጋር ተያይዞ በተነሳው አስተያየት፤ የውሃ መስመር ቁፋሮ እና የመሰረተ ልማት ሥራዎች ሲከናወኑ በቂ ጥንቃቄ ካልተደረገ ጉዳት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ተመላክቷል። 

በተለይም የውሃ ማሽኖች ወይም መስመሮች በሚሰሩበት ወቅት የውሃ አቅርቦት መቋረጥ እና ከፍተኛ ግፊት ያለው ውሃ መፈንዳት በነዋሪዎች እንቅስቃሴና በአካባቢው ንብረት ላይ ስጋት የሚፈጥር መሆኑ ተጠቁሟል።

በዚሁ በዎላይታ ሶዶ ከፍተኛ ግፊት ያለው የውሃ ቧንቧ መፈንዳት ምክንያት በዩንቨርስቲ ሰፈር የውሃ አገልግሎት መቋረጥ መፈጠሩንም WT Media ከነዋሪዎቹ አረጋግጧል።

በአካባቢው የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት ግንባታና ጥገና ሥራዎች ሕዝብን ለአደጋና ለአገልግሎት መቋረጥ በማይዳርግ መልኩ በጥንቃቄ እንዲከናወኑ ማህበረሰቡና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አስተያየቱ ያመለክታል።