የዎላይታ ልማት ማህበር

በሀገር ውስጥም ሆነ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ ዜጎችና ደጋፊዎች የዎላይታ ልማት ማህበር (ዎልማ) አባል መሆን እና ዲጂታል መታወቂያ ማግኘት የሚችሉበት ኦንላይን (በድረ-ገጽ በኩል) የምዝገባ አሰራር ይፋ ተደርጓል።

ይህ አሰራር ማህበሩ በሰብአዊነት እና በልማት ስራዎች የሚያከናውናቸውን እንቅስቃሴዎች ለመደገፍና በአባልነት ለመሳተፍ ለሚፈልጉ አካላት ያሉበት ቦታ ሳይገድባቸው በቀላሉ መመዝገብ የሚችሉበትን መንገድ የሚያመቻች ሲሆን ምዝገባው በሚከተሉት ቅደም ተከተሎች እንደሚከናወን ተገልጿል።

የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ቅደም ተከተሎች

  1. በስልክ ወይም በኮምፒውተር እንደ Google Chrome ወይም Mozilla Firefox ያሉ የኢንተርኔት ብሮውዘሮችን መክፈት።
  2. የዎላይታ ልማት ማህበር ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ አድራሻ ([https://wolaittada.org.et) ወይም ቀጥታ የምዝገባ ገጽ ([https://wolaittada.org.et/member-registration](https://wolaittada.org.et/member-registration)) መክፈት።
  3. በድረ-ገጹ ላይ «Get Involved / ተሳትፎ» የሚለውን በመጫን ከስሩ «Membership Registration» የሚለውን መምረጥ።
  4. በምዝገባ ቅጹ ላይ የሚጠየቁ ትክክለኛ የግል እና ተያያዥ መረጃዎችን በአግባቡ ማስገባት።
  5. የ3×4 መጠን ያለው ጉርድ ፎቶ (Photo) ስርዓቱ ላይ መጫን (Upload ማድረግ)።
  6. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000018167569 የፕላቲኒየም አባልነት ክፍያ 1,200 ብር ገቢ በማድረግ የክፍያውን ማረጋገጫ የFT ቁጥር በተዘጋጀው ቦታ መጻፍ።
  7. የክፍያ ደረሰኙን ስክሪንሾት (Screenshot) በሚጠይቀው ቦታ ላይ በማስገባት መረጃውን ማረጋገጥ እና Submit በማለት ምዝገባውን ማጠናቀቅ።

ምዝገባው በኦንላይን ከተጠናቀቀ በኋላ የቀረቡት መረጃዎችና የክፍያ ማስረጃዎች በዎላይታ ልማት ማህበር ድረ-ገጽ አስተዳዳሪ (Admin) ተረጋግጠው ሲጠናቀቁ ዲጂታል መታወቂያው ለተመዝጋቢው እንደሚደርስ ማህበሩ አስታውቋል።

የዎላይታ ልማት ማህበር የዲጂታል አባልነት ምዝገባ ስርዓት በድረ-ገጽ በኩል መዘጋጀቱ በሀገር ውስጥም ሆነ ከየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ ዜጎችና ደጋፊዎች ያሉበት ቦታ ሳይገድባቸው በቀላሉ እንዲሳተፉና አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችል አሰራር ሆኖ ቀርቧል። አባል መሆንና ዲጂታል መታወቂያ ማግኘት የሚፈልጉ አካላት የተቀመጡትን መስፈርቶችና የክፍያ ሂደቶች በማሟላት በራሳቸው ፈቃድና ውሳኔ የሚከውኑት ጉዳይ ስለመሆኑ WT Media ባደረገው ማጣራት አረጋግጧል።

ዎልማ በ1950ዎቹ እ.ኤ.አ. የተመሰረተ ሲሆን በዎላይታ እና ከአካባቢው ባሻገር ዘላቂ ልማትንና የማህበረሰብ አቅምን ማሳደግን ለማስፋፋት የሚሰራ ሀገር በቀል፣ ለትርፍ ያልቆመ እና በአባላት ላይ የተመሰረተ የአካባቢ ድርጅት ነው። ከተቋረጠና ከተደራጀ በኋላ በ1993 ዓ.ም. ሙሉ በሙሉ እንደገና የተቋቋመ ሲሆን፣ ከታህሳስ 2000 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ደግሞ በወላይታ ዞን የሚገኙ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ተቋማዊ ችግሮችን የሚፈቱ የተቀናጁ የልማት ፕሮግራሞችን በንቃት በመተግበር ላይ ይገኛል።

ራዕዩን ህብረተሰቡን ከኋላቀርነት እና ከድህነት ተላቆ ማየትን፤ ተልዕኮውን ደግሞ ከማህበረሰቡ፣ ከመንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከደጋፊዎች እና ከሌሎች ምንጮች ሀብት በማሰባሰብ እንዲሁም በሰው ሀብት ልማት፣ በዘላቂ የኑሮ ዋስትና እና በተቀናጀ ጤና ዘርፎች በፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የልማት ፕሮግራሞችን በመጀመር እና የነቃ የማህበረሰብ አገልግሎትን በማሳደግ ለዎላይታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ቁርጠኛ ሆኖ መስራት ማድረጉን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ማህበሩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዘንድ በምዝገባ ፍቃድ ቁጥር 0486 ህጋዊ ምዝገባ ያለው ሲሆን ዋና መሥሪያ ቤቱ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ይገኛል። በሁሉም የዎላይታ ዞን ወረዳዎችና ከተሞች የስራ ማስፈጸሚያ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ያሉት ሲሆን በአዲስ አበባ፣ ሀዋሳ፣ አርባ ምንጭ፣ ሻሸመኔ፣ ዲላ፣ ሀዳሮ፣ መተሃራ፣ አሚባራ እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች ተወካይ ቢሮዎች፣ በኬንያ ናይሮቢ ደግሞ ህጋዊ ቅርንጫፍ አለው።

WT Media እንደ የተገለሉ ማህበረሰቦች ድምፅ በመሆኑ በልማት፣ በማህበራዊ ተሳትፎ እና በህዝብ አገልግሎት ዙሪያ የሚወጡ የአሰራር መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ከማድረስ ባለፈ የአባልነት ምዝገባን በተመለከተ ቀጥተኛ የውሳኔ ወይም የማስተዋወቅ ሚና ሳይኖረው፣ ዜጎች ትክክለኛ መረጃ ይዘው የራሳቸውን ውሳኔ እንዲወስኑ በገለልተኝነት መረጃውን ማቅረቡን ይቀጥላል።