የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈጻሚ ግብረ ኃይል አደረጃጀትና ወቅታዊ ሁኔታ ዙርያ የዎላይታ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ
አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅታዊነቱን የጠበቀና አገርን ከቀውስ ለማዳንና አከባቢን ለመጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ ለተግባራዊነቱም በመረባረብ የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል 10 ሻለቃ አዛዥ ኮማንደር ፈለቀ ፈለሃ ተናግረዋል።
የዎላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢ/ር ጎኣ ከሣ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ እና ኢ መደበኛ አደረጃጀት ፈጥረው ህብረተሰቡን በሃሰተኛ መረጃ መንግስት ላይ አመኔታ እንዳይኖር የሚሠሩ አካላት ላይ በተገቢው መረጃዎችን በማደራጀት ህግ የማስከበር ሥራ በተገቢው መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል።
ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩና የሚያሸብሩ አካላትን ለመቆጣጠርና በህግ አግባብ እንዲጠየቁ ለማድረግ፣ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር በማድረግ ያልተመዘገቡ ጦር መሣሪያዎች የማስመዝገብ ፣ በመደበኛ ህግ ብቻ ከመቆጣጠር ይልቅ ተጨማሪ አዋጅ አስፈላጊ በመሆኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስከታች ድረስ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የዎላይታ ዞን ሠላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጎኣ ገልጸዋል።
እንደ መኮጉ ዘገባ መረጃ አደረጃጀት እና የተደራጀ መርጃ በተገቢው ትርጉም ሰጥቶ በመተንተንና በህግ አግባብ ላይም ብዥታ በማይፈጥር መልኩ የጸጥታ መዋቅሩ በትኩረት እንደሚሠራ የመምሪያ ኃላፊው ጠቁመዋል።
መረጃ መር የወንጀል መከላከል ሥራና ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ፍታዊ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ልሰጥ እንደሚገባና የአዋጁ አፈጻጸምና ተግባራዊነት በሂደት እንደሚሆን ተጠቁሟል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 26/02/14 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹