በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማና የይርጋጨፌ ወረዳ ነዋሪዎች አሸባሪው የህወሃት ጁንታ በሀገራችን እያካሄደ ያለውን ወረራና የሽብር ተግባር የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ሠልፈኞቹ በፕሮፓጋንዳው ጦርነት አንበገርም፣ ለቀረበልን የክተት ጥሪ በህዝባዊ ቁጭትና ፅናት ተሰልፈናል፣ የተከፈተብንን የክህደት ጦርነት ለመቀልበስ በፅናት ተሰልፈናል፣ ሸኔ የህወሃት ተላላኪ ነው፣ የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች በማስደመጥ ላይ ይገኛሉ።


