የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪን ጨምረው ሌሎችም ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

ህብረተሰቡ ለሀገር ህልውና የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል።

በዛሬው ዕለት በዎላይታ ዞን አመራሮችና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ ድጋፋቸውን አሳይቷል።

በዞኑ ከደም ልገሳ ፕሮግራም በተጨማሪ ህብረተሰቡ ለመከላከያ ሰራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ መጠናከር እንደሚገባና አከባቢውን ከሰርጎ ገቦች በመጠበቅ የድል ዜና እስኪሰማ ከፀጥታ ጎን በመቆም መጠበቅ እንደሚገባ ተገልጿል።