
የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች ምላሽ ስሰጡ ተመካክረን፣ ተነጋግረንና ተወያይተን ለጋራ ዓላማችን ከቆምን ዘላቂ ሠላምንና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንችላለን ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው የተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ችግሮችን በተጨባጭ ለመመለስ በየደረጃው ያለው አመራሩና ህዝቡ ድርሻቸውን ወስደው ልተገበሩ ይገባል ብለዋል፡፡
በድህነት እስራት ዉስጥ ያለን ህዝባችንን ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማሸጋገር የሚንተኛበት ወቅት ላይ አይደለንም ነው ያሉት፡፡
ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ ህብረተሰቡ ከፀጥት አካላት ጋር በመሆን አከባቢውን በንቃት መጠበቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የኑሮ ዉስድነት ችግር ለመቅረፍ በየአከባቢው ያለውን የዉሃ አመራጮችን ተጠቅመን ምርትና ምርታማነቱን መጨመር ከቻልን የዋጋ ንረቱን መቀንስ እንችላለን ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
ለዚህም አመራሩና ባለሙያው በኃላፊነት መንፈስ መመራትና መረባረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ተምረው ሥራ አጥተው ቤት ቁጭ ያሉ ወጣቶች ችግር ከፍተኛ እንደሆነ የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው የቻለነውን አቅም ሁሉ በመጠቀም ወጣቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት በቁጭት ሊንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
አያይዘዉም የሥራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ የትኛውንም ዕድል መጠቅም አለብን ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ከፈዴራልና ከከልል መንግስትም ጋር በመቀናጀትና በመናበብ እንሰራልን ብለዋል፡፡
በየአከባቢው እየተሰሩ ያሉ የልማትና የመሠረት-ልማት ሥራዎች በጥራትና በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ የመከታተልና የመደገፍ ሥራ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ከጤና ዘርፍ አንጻር የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ ና የመድኃኒት አቅቦት ችግርን ለመፍታት በአቋም ይዘን መምራት አለብን፡፡
በግብርና ልማት በዘንድሮ በልግ እርሻ ሥራ በሽታ የማያጠቃውን የኢንሰት ዝሪያዎችን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ እንዲሆን አጠናክረን መሰራት አለብን ብለዋል፡፡
በየተቋማቱ ህዝብረተሰቡን የሚያማሪሩ አግልግሎት አሰጣጥ ችግርችን በዘላቂነት ለመፍታት ስነ-ምግባር የጎደሉና አግልግሎቶችን በገንዝብ ለመስጠት ሚፈልጉ ግለሰቦችን አመለካከትን መቀየርና በዲሲፕልንም ጭምር ተጠያቅ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት፡፡
ህብረተሰቡ አልቅሰውና ለምነው የሚያገኙት አገልግሎት እንዲቀረፍ ሁሉም የድርሻውን ልዎጣ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የህዝባችንን ሁለንተናዊ ብልጽግናን እንዲረጋገጥ እጅ ለእጅ ተያይዘን፤ አንድነታችንን አጠናክረን መሠራት ከሁላችንን ይጠብቅብናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ተመካክረን፣ ተነጋግረንና ተወያይተን ለጋራ ዓላማችን ከቆምን ያለን አቅማችንና ጉልበታችን ተጠቅመን ምቹ ሀገር መፈጠር እንችላለን ሲሉ አስታውቀዋል፡፡