የቀድሞ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እንዲሁም ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች የነበሩና ሌሎች ተከሳሾች በዛሬው ዕለት በክልሉ ተዘዋዋሪ ችሎት በአርባምንጭ ቀርበዋል።

እስካሁን የተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ ተመስገን ዋጃና ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የዛሬውን ችሎት በተመለከተ በሰጡት መረጃ መሠረት በዛሬው ዕለት ችሎቱ በተካሳሾች ላይ በተነሳው ክስ ጭብጥ ላይ ዳኞች የምስክርነት ቃል መቀበላቸውን ተናግረዋል።

አሁን ላይ በሌላ ወንጀል ተጠርጥረው በማረሚያ ተቋም የሚገኙ የቀድሞ የፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታፈሴ ምስክርነት ስሰጡ “አመራሮቹ ከህዝብና ከመንግሥት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ተወጥተዋል እንጂ ወንጀል ሰርተዋል ማለት አልችልም” በሚል ምስክርነታቸውን መስጠቱን ጠበቃ አቶ ተመስገን በተለይም ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ከዚህ በፊት በዞኑ በተከሰተው አለመረጋጋት ወቅት የነበሩ መከላከያ ሰራዊቶች በተከሳሾቹ ላይ የሰጡት ምስክርነት ውድቅ እንዲሆን ጠበቃ አቶ ተመስገን ችሎቱን መጠየቁን አብራርተዋል።

ያንን መነሻ በማድረግ ፍርድቤቱ ” ህገመንግስታዊ ስራዓትን በኃይል መናድ በሚል ለተከሰሱ ተከሳሾች ብይን ለመስጠት ለሚያዚያ 11/2014 ዓ.ም ቀጠሮ መያዙንም ጠበቃቸው አቶ ተመስገን ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: