ከጎንደር ዩንቨርስቲ ከሰባት በላይ የቀድሞ የዎላይታ ሊቃ ተማሪ የነበሩ የህክምና ዶክተሮች በከፍተኛ ውጤት ተመረቁ

ጎንደር ዩኒቨርስቲ ጤና በዛሬው ዕለት ካስመረቀው 334 ተማሪዎች መካከል ከሰባት በላይ የቀድሞ የዎላይታ ሊቃ ተማሪ መሆናቸው ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት ማለትም ሰኔ 25/2014 ዓ.ም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለይም የቀድሞ የዎላይታ ሊቃ ተማሪ የነበሩ ዶክተር ፀጋዬ ከበደ፣ ዶክተር ዳግማዊ ዳዊት፣ ዶክተር ናርዶስ ቶማስ፣ ዶክተር አድሱ ቦኔ፣ ዶክተር ጥበቡ ዳንኤል፣ ዶክተር ሳምሶን ወ/ሰንበት ከዩኒቨርስቲ በከፍተኛ ውጤት መመረቃቸውን ከቀድሞ ሊቃ ተማሪዎች የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በመርሃ ግብሩ  የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ ፣ የማዕከላዊ ጎንደር ዋና አስተዴሪ አቶ ወርቁ ኃ/ማርያም ፣ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ የአርማውር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት  ዋና ዳይሬክተር፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን፣ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እና የተመራቂ ወላጆች በተገኙበት  በዓሉ መከናወኑን ከዩንቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: