የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ “ማስታወቂያ ቦርድ” በዎላይታ ሶዶ ከተማ አገልግሎት መስጠት ጀመረ!!

ከዲጂታል ማስታወቂያ በተጨማሪ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን በተደራጀ አግባብ ለማግኘት “የሥራ ማስታወቂያ ቦርዱ” ያስችላል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከ SNV #RAYEE Ethiopia የተባለ አለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት ከMastercard Foundation ጋር በመተባበር ይህን የስራ ማስታውቂያ ቦርድ በከተማዋ አማካይ በሆኑ ሶስት ቦታዎች ላይ በይፋ አስጀምሯል።

በከተማው የሚስተዋለውን ህገወጥ የስራ ማስተውቂያ አሰራርን በማስቀረት ፍትሃዊ የማስታወቂያ ተደራሽነትንና አገልግሎትን በጥራትና በቀላሉ ተግባራዊ ለማድረግ አስቻይ መሆኑም ተጠቁሟል።

በከተማው ሆነ በአከባቢው ህጋዊ የስራ ማስታወቂያ ቦርድ ባለመኖሩ ህብረተሰቡ በተለያዩ ቦታዎች ባልተደራጀ ሁኔታ የሚለጠፉ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን የማግኘት ዕድል አነስተኛ በመሆኑ ለተጠቃሚዎች እንቅፋት ሆኖ መቆየቱና ማስታወቂያ ለመለጠፍ ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ሲለጠፍ ለከተማ ውበት ማነቆ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

ከዚህ በፊት የተለያዩ የስራ ማስታወቂያዎች በተለይም የጨረታ ማስታወቂያዎች፣ የፍርድቤት ጥሪ ማስታውቂያዎች እና ሌሎች ማስታወቂያዎች በከተማዋ በተደራጀ ሁኔታ «በማስታወቂያ ቦርድ» ባለመለጠፉና ተገቢ ጥበቃ ስለማይደረግ ብዙ ችግር ሲያስከትል ቆይቷል።

በዋናነትም ህጋዊነት ባልተከተለ መልኩ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ለተጠቃሚዎች ሳይደርስ የመበላሸት፣ የመቀደድ እናም ሆን ተብሎ ያለግዜ የመነሳት ሁኔታዎች የተስተዋለ ሲሆን፤ ድርጅታችን የጀመረው የተደራጀ የስራ ማስታወቂያ ቦርድ ችግሩን ይቀርፋል ተብሎ ይታመናል።

ድርጅታችን በሶዶ ከተማ ለህብረተሰቡ በቀላሉ ተደራሽ በሚሆኑ ሶስት ቦታዎች ላይ(በአበበ ዘለቀ እንተርናሽናል ሆቴል ፊትለፊት፣ በቀሌ ሞላ ሆቴል ፊትለፊት እንዲሁም በዎላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ዋና መግቢያ በር ፊትለፊት) ከሚመለከታቸው አካላት ህጋዊ ፈቃድ በመወሰድ ስራውን በይፋ ተጀምሯል።

ይህ ተግባር ከማስታወቂያ አገልግሎት ጎን ለጎን የተለያዩ የጨረታ ጋዜጦች፥ ማጽሄቶችን እና መጽሃፍትን በቀላሉ የሚያገኙበት ሁኔታ ያመቻቸ ሲሆን በዚህም እስከ ስድስት ለሚደርሱ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጥሯል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የስራ ማስታውቂያ ቦርድ (Offline Job Board) በተጨማሪ በሚዲያው ዌብሳይ እና ማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቋሚ ማስታውቂያ ቦርድ (Online Job Board) አማራጭ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጀቱን ጨርሷል።

የተለያዩ ማስታውቂያዎች ተደራሽ እንዲሆን የሚፈልግ ማነኛውም መንግስታዊ ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንዲሁም ግለሰብ ከዛሬ ጀምሮ ከታች በተጠቀሱ ስልኮቻችን በመጠቀም ህጋዊ በሆነ መንገድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል እየገለፅን፤ የትኛውም አካል ማስታውቂያ ለመለጠፍ ባልተፈቀደ ቦታ ላይ መለጠፍ እንደማይችል እየገለፅን ይሄ ስራ እውን እንዲሆን እገዛ ያደረጉ SNV #RAYEE Ethiopia የተባለ አለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅት እና Mastercard Foundationን የWT ሚዲያ ማኔጅመንት ያመሰግናል።

👉0913839171
👉0953750517 በመደወል ህጋዊ በሆነ መንገድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ🤲

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *