በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የታሪክና ገድላት ድርሳናት ውስጥ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጣቸው የዎላይታው ንጉሥ ሞቶሎሚ እና የአቡነ ተክሌሀይማኖት ታሪካዊ ትስስር ምንድነው❓

በዎላይታ ዞን ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አጆራ ቀበሌ በሚገኘወና የምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው
የአጆራ መንትያ ፏፏቴዎች ላይ የዛሬ 800 ዓመታት አካባቢ ከታች በፎቶ የሚታየው የፃድቁ አባት የንጉስ ሞቶሎሚ ልጅ የአቡነ ተክለሃይማኖት እናት ቅድስት እግዛሪያንን በወቅቱ የዎላይታ ገናና ንጉስ ሞቶሎሚ በሰርግ ያገባበት እና ፃድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የተፀነሱበት ታሪካዊ ስፍራ መሆኑን የተለያዩ የታሪክ ድርሳናት ይመሰክራሉ።

ቅድስት እግዛሪያን በዎላይታ አካባቢ “ሳራ” የምትባል ሲሆን አቡነ ተክለሃይማኖት ደግሞ “ሹሙሩኮ” ተብሎ ይጠሩ ነበር::

ይህንን ታላቅ ትውፊታዊ ገድል እና ሌሎች የታሪክ ድርሳናትን ስናይ የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት እናት እግዘሪያ በንጉሥ (ካዎ) ሞቶሎሜ ወታደሮች ተማርከው ወደ ዎላይታ የንጉሡ ቤተመንግሥት መቀመጫ ወደሆነው ወደ ዳሞት ተራራ እንደመጡና ከንጉሡ ጋር ለአያሌ ቀናት ከቀዩ በኃላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው እንደሄዱ፣ እግዘሪያ በንጉሡ ወታደሮች ስማረኩ ቄስ የሆኑት ባላቸው ፀጋዘአብ መኻን በመሆናቸው ልጅ እንዳልነበራቸው እና ከምርኮ ስመለሱ ከንጉሥ ሞቶሎሜ አርግዘው ስለነበረ አቡነ ተክለሃይማኖትን እንደወለዱ ይገልጻል።

ይህ ግዜ ልክ የዛሬ 756 አመት አካባቢ ሲሆን አቡኑ አድገው ከጎለመሱ በኃላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የክርስትና እምነት ለንጉስ ሳሶ ሞቶሎሚና ለሕዝቡ ለማስተማር ብለው ከቡልጋ ወደ ዎላይታ እንደገቡ በታሪክና በአዛውንቶች ይነገራል::

ጳጳሱ ለስብከት ስራቸው ወደ ተራራው ጫፍ ማለትም ወደ ንጉሱ ቤተ መንግስት የሚመላለሱበት መንገድ ከጋራው እግርጌ በስተደቡብ ከዳርና-ጉብታ በኩል በነበረው ጠመዝማዛ፣ አድካሚ ዳገትና ቀልቁለት በመውረድና በመውጣት ተመላልሰው ነበር የሰበኩት::

ከታች ወደላይና ከላይ ወደ ታች በእግር ጉዞ ወቅት ሲደክማቸው አርፈው የሚፀልዩበትን ዘወትር የሚመላለሱበትን መንገድ የአካባቢው ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ የእግዜአብሔር መተላለፊያ(ጦሳ ፔንግያ) በማለት ይጠሩታል::

የስያሜውን ምክንያትም ሲነግሩ የአቡነ ተክለሃይማኖትና የመነከሴዎቹ መመላለሻና መተላለፊያ ስለነበረ፣ እነሱንም ሕዝቡ እንደጻድቅ ስለሚቆጥራቸው ይኸው የተመላለሱበት ያረፉበት ቦታ የእግዜአብሔር መንገድ ተብሎ ሊጠራ ችሏል::

የገድለ አቡነ ተክለሃይማኖት ታሪክ ቃል በቃል እንደሚለው ከሆነ “የመኻኑ ፀጋዘአብ ምሽት እግዘሪያ በምርኮ ወደ ዳሞት ቤተመንግሥት ከተጋዘች ከአስራ አምስት ቀናት ቆይታ በኃላ መልአኩ ሚካኤል በመጋቢት 24 ቀን ሌሊት ከዎላይታ ከካዎ ሞቶሎሜ ቤተመንግሥት ወደ ቡልጋ መለሳት” ይላል። መጽሐፉ ለጥቆም፣ “ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ታህሳስ 24 ተወለዱ” ይለናል።

የተፈጥሮ ሳይንስ እንደሚለን ከሆነ አንድ ጤናማ ልጅ ለመወለድ በእናቱ ማሕፀን ውስጥ ዘጠኝ ወርከ አስራ አምሰት ቀን ይቆያል። እንግዲህ እነዚህን ትውፊታዊና ተፈጥሯዊ ሐቆችን ደምረን ስናካፍል፣ አውጥተን ስናወርድ እና በአናቱም ላይ የፀጋዘአብን በመጽሐፉ የተረጋገጠ መኻንነትን ስንጨምርበት አቡነ ተክለሃይማኖት የማን ልጅ እንደሆኑ ማረጋገጫ litmus paper መጠቀም የሚያሻ አይደለም።

አቡነ ተክለሃይማኖት በኢትዮጵያ ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ሐይማኖት ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በ957 ዓ.ም ገደማ በዪዲት ጉዲት የፈረሰውን የኢትዮጵያዉን ‘Solomonic Dynasty’ ከ333 ዓመታት ቆይታ በኃላ መልሰው በጊዜው የአስራ ሁለት ዓመት ታዳጊ ለነበረውና ከሰለሞን ዘር ለተወለደው ለይኩኖአምላክ አሳልፎ የሰጡት ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ናቸው።

ለዚሁ ውለታቸው ስባልም አፄ ይኩኖ አምላክ በንግስናቸው ዘመን የግዛታቸውን አንድ ሶስተኛ ወይም ስሶ አቡኑ በፓትርያርክነት ለሚመራቸው ቤተክርስቲያን እንዲሰጣት ወስኗል። ይኽም ውሳኔ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በቤተመንግስትና በቤተክርስቲያን መካከል ፀንቶ ቆይቷል ስል የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *