ዎላይታ ዲቻ ሲዳማ ቡናን አንድ ለባዶ አሸነፈ

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ 13ኛ ዙር ጨዋታ ወደ ባህርዳር ከተማ አቅንተው የሲዳማ ቡና አቻውን የገጠሙት የጦና ንቦች ከሜዳ ውጭ ድል ቀንቷቸዋል።

በጨዋታው የጦና ንቦች በሁለተኛ አጋማሽ በአናገው ባደገ በ49′ ደቂቃ የማሸነፊያ ጎል ያስቆጠሩ ሲሆን በዚሁም የደረጃ ለውጥ አድርጓል።

ዎላይታ ዲቻ በተላይም በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ አከባቢ የውጤት ቀውስ ውሰጥ በመግባቱ ከደጋፊዎች ብርቱ ተቃወሞ በመነሳቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥቶ የተለያዩ ማስተካከያ እርምጃዎችን በመውሰዳቸው ጥሩ የውጤት መሻሻል እያሳዩ ይገኛሉ።

FT Wolaita Dicha 1_0 Sidama Buna