fff

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን የአፕል ፍሬ ለምን ይቀበራል ያለው የግብርና ባለሙያ ታሰረ

በጋሞ ዞን የጨንቻ ግብርና ባለሙያ የሆነው አቶ ብርሃኑ ጨርቆስ የተባለ ግለሰብ በማህበራዊ ሚዲያ ለምን የአፕል ፍሬ ለምን ይቀበራል ብሎ አስተያየት በማጋራቱ መታሰሩን ከስፍራው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ሁኔታው የመረጃ ምንጩ ሲገልፅ “ግዘው ሳይደርስ አፕል እንዳይለቀም ተባለ። ከዛም የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ና ትራስንፖርት ጽ/ቤት 700KG አፕል ሰብስበው ይቀብራሉ። የጨንቻ ከተማ ግብርና ጽ/ቤት የግብርና ባለሞያ የሆነው ብርሃኑ ጨርቆስ ጫቶ አፕል ከምቀበር ተሽጦ ለቤት እንስሳት መኖነት ብውል ይጠቅማል” የምል ሀሳብ በማንሳቱ ዋስትና ተከልክሎ ይገኛል” ብሏል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በጋሞ ዞን የጨንቻ ከተማ ከንቲባ አቶ ደመላሽ ንጉሴን በእጅ ስልካቸው ለማግኘት የደወልን ቢሆንም ምላሽ ባለመስጠታቸው ምላሽ ማካተት አልተቻለም።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌

👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏

👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀#WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia#southethiopia