በዎላይታ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የዘንድሮው በልግ አፈፃፀምና በመኸር ቅድመ ዝግጅት ሥራ ዙርያ የንቅናቄ መድረክ ጀመረ።

የ2013 ዓ.ም በልግ አፈፃፀምና የመኸር ዕቅድ ዝግጅ እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች እየተካሄደ ይገኛል።

በእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት በሁሉም ዘርፎች የተሠሩ የዓመቱ ሥራዎች፣ የበልግ አፈጻጸም፣ የመኸር ዕቅድ ዝግጅት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት መካሄዱ ተገልጿል።
 
በምክክር መድረኩ የዞን፣ የወረዳው አስተባባሪዎች ፣ መካከለኛ  አመራሮች ፣ የቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የግብርና ባለሙያዎችና የየቀበሌ አስተዳዳሪዎች እንድሁም በሁሉም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ መሆኑን ለWT ከየቦታው የደረሰው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://youtube.com/wolaitatimes/ በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 05/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹