በተለይም ለWolaita Times ሚዲያ ከስፍራው አሁናዊ መረጃ ደርሷል።
ከኢትዮጵያ በተለይ ከደቡብ ክልል አካባቢ በርካታ ዜጎች ኑሮአቸውን ለመቀየር መዳረሻ ደቡብ አፍሪካን ቀዳሚ ሀገር ማድረጋቸው ይታወቃል።
ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ሰሞኑን በሀገሪቱ በተከሰተው ግጭት ምክንያት እዚያው በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ንብረት ላይ ዘረፋ እና ጉዳት እንደደረሰ ከስፍራው በስልክ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ስሙን ለመጥቀስ ያልፈለገው አንድ በጇዋንስበርግ ከኢትዮጵያ ደቡብ ክልል ከዎላይታ አካባቢ ሄደው ለአምስት አመታት እዚያው የቆየው እንደገለፀው ሁኔታው አሳፋሪ እና በምንም ተቀባይነት የለለው መሆኑን ገልጿል። “እኛ ሰርተን ደክመን ያገኘነውን ንብረት በደቂቃዎች ውስጥ ማጣት እጂግ ያማል፣ በህይወቴ ዘመን እንደዚህ አይነት አሳፋሪ ነገር አይቼ አላውቅም” ብለዋል።
ሌላኛው ከጇዋንስበርግ አስራ አምስት ኪ.ሜ በሚትገኘው ካስሞ በምትባል ከተማ ኑሮን ያደረገውና ከሀዲያ አከባቢ የሄደው አቶ በረከት ላቾሬ በሱቅ ውስጥ የነበረውን ንብረት በቡድን የመጡ ዘራፊዎች እንደወሰዱት ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ለዜጎች ጥበቃና ከለላ የሚያደርግበት መንገድ እንዲያመቻችላቸውም አቶ በረከት ጠይቀዋል።
አቶ ደጉ ዳቼ ራስተንበርግ ከተማ የሚኖር ሲሆን በተከማዋ እስካሁን ምንም አለመከሰቱን ገልፀው በተጨማሪም አንዳንድ ግጭቱ ያልደረሰባቸው ከተሞች ቢኖሩም የመስፋፋት ዕድል ልኖር ስለሚችል የኢትዮጵያ ኢምባሲ በቅርበት መከታተል እንዳለበት አሳስበዋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የጥንቃቄ ስራዎችን በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁ የሚታወቅ ሲሆን በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ትብብር እያደረጉ መሆኑን ቢገልፁም በዛሬው እለት ከሰማሌ ክልል የሆዱ ኢትዮጵያዊያን በብዛት በሚኖሩባት ስያ በምትባል ከተማ የጓዋደኛ ንብረት ጨምረው በሰፋት ዘረፋ መፈፀሙንና አስካሁን ባለው መረጃ በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰ የአካል ሆነ የህይወት ጉዳት አለመኖሩን አቶ ደጉ ዳቼ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በስልክ አብራርተዋል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://youtube.com/wolaitatimes/ በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 07/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹