የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት “ከአድሏዊ ፖለቲካ ተግባር በተጨማሪ ለሰብዓዊነት በሚውል የሰው ደም በመስረቅ ጭምር ኢፍትሃዊነትን በአደባባይ እያሳዩ ነው” ተባለ
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እና የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ፣ ከብሔራዊ ደም እና ሕብረ-ሕዋስ ባንክ ጋር በመተባበር የደም መመርመሪያ ማሽንን ወደ አርባ ምንጭ በማዞር በዎላይታ በሌሎች ሕዝብ ላይ ጥላቻ በተሞላበት ሴራ ፖለቲካ ውስጥ እየተሳተፉ ነው ሲል WT ሚዲያ ከደረሰው መረጃ ገልጿል።
የዚሁ ከፖለቲካ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው የጤና ጉዳይ ላይ ጭምር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ያሳዩት “ጫፍ የወጣ ኢ-ፍትሃዊነት ተግባር” ማሳያ የተባለ ሲሆን ይህ ውሳኔ በበርካቶች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታንና ግርምትን ፈጥሯል።
እንደ መረጃው ከሆነ፦ የብሔራዊ ደም እና ሕብረ-ሕዋስ ባንክ በመጀመሪያ ዙር ስድስት ዘመናዊ የደም መመርመሪያ ማሽኖችን ለተለያዩ ክልላዊ ከተሞች፣ ከእነዚህም መካከል መቀሌ፣ ባህርዳር፣ አዳማ፣ ጅግጅጋ፣ ሀዋሳ እና አዲስ አበባ ይገኙበታል። እነዚህ ማሽኖች ባለፉት ሦስት ዓመታት ከፍተኛ ደም ለጋሾች ባሉባቸው አካባቢዎች ምርመራዎችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል።
ሁለተኛው ዙር ማሽኖች እና አወዛጋቢው ውሳኔ
አሁን ደግሞ በሁለተኛው ዙር የገቡት ማሽኖች ለቀሪዎቹ ክልላዊ ከተሞች እንዲላኩ ዝግጅት በተጠናቀቀበት ወቅት፣ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ማሽኑ ወደ አርባ ምንጭ እንዲሄድ እያደረጉት እንደሆነ WT ሚዲያ ዘግቧል።
ይህን “እኩይ ተግባር” ለማስረዳት የተሰጡት ምክንያቶች:
የሶዶ ደም ባንክ ሕንፃ ግንባታ አለመጠናቀቁ።
የደም ባንኮች አፈፃፀም።
የአየር ማረፊያ በአርባ ምንጭ መኖሩ ይላሉ።
ሆኖም ግን WT ሚዲያ ከደረሰው መረጃ እንደተገነዘበው እነዚህ ሦስቱም ምክንያቶች ከእውነታ የራቁ እና ለማነፃፀር የማይበቁ ናቸው።
የቀረቡት ምክንያቶች ምላሽ
1. የሶዶ ደም ባንክ ሕንፃ ግንባታ
የሶዶ ደም ባንክ ሕንፃ ግንባታ የተጀመረው በ2010 ዓ.ም አቶ አቅናው ካውዛ የጤና ቢሮ ኃላፊ በነበሩበት ጊዜ ነው። አቶ እንዳሻው ሽብሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ግን ግንባታው ሆን ተብሎ እንዳይጠናቀቅ የተለያዩ ምክንያቶችን በመጥቀስ ክፍያዎችን በማዘግየት ግንባታው ለሰባት ዓመታት ያህል ሳይጠናቀቅ እንዲቆይ አድርገዋል የሚል መረጃ ለWT ሚዲያ ደርሷል።
2. የደም ባንኮች አፈፃፀም
የአርባ ምንጭ ደም ባንክ ከስድስት ዞኖች ደም የሚሰበስብ ሲሆን፣ ሁለት መኪና እና 15 የጤና ባለሙያዎችን ይዞ ዓመታዊ ዕቅዱ 9000 ዩኒት ደም ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 5500 ዩኒት ደም መሰብሰቡ ተገልጿል።
በሌላ በኩል፣ የዎላይታ ሶዶ ደም ባንክ ከአንድ ዞን ብቻ ደም የሚሰበስብ ሲሆን፣ አንድ መኪናና 12 የጤና ባለሙያዎችን በመጠቀም ዓመታዊ ዕቅዱ 8000 ዩኒት ደም ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 4350 ዩኒት ደም ሰብስቧል።
ብዙ ዞኖችን፣ በርካታ መኪናዎችን እና ባለሙያዎችን ይዞ ከሚሰራ ደም ባንክ ጋር፣ በአንድ ዞን ብቻ የሚሰራን ደም ባንክ ማነፃፀር “ሕዝብ ይፍረድ!?” የሚያስብል ኢ-ፍትሃዊነት ነው ሲል መረጃው ይጠቁማል።
3. የአየር ማረፊያ በአርባ ምንጭ መኖሩ
የአየር ማረፊያ በአርባ ምንጭ መኖሩ ከደም ምርመራ ጋር ምንም ዓይነት ቀጥተኛ ግንኙነት እንደሌለው ለWT ሚዲያ በደረሰው መረጃ ተገልጿል።
ምናልባት ማሽኑ ቢበላሽ ከአዲስ አበባ ቶሎ ለመድረስና ለመጠገን የሚጠቅም ነው የሚለው “የድኩማን አስተሳሰብ” ካልሆነ በስተቀር፣ ማሽኑን ለሚያንቀሳቅሱ ባለሙያዎች ልዩ የጥገና ሥልጠና እንደሚሰጥ ከአዲስ አበባ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የዎላይታው አየር ማረፊያ ግንባታ ቢሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ሆን ብለው እንዲጓተት በማድረግ ላይ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው።
ማሽኑን በዎላይታ መትከል ለሌሎችም ጭምር ያለው ጠቀሜታ
ማሽኑን በዎላይታ መትከል ለዎላይታ ብቻ ሳይሆን ለአጎራባች አካባቢዎች እንደ ሆሳዕና፣ ሃላባ፣ ሀዋሳ፣ ሳውላ፣ ሻሸመኔ፣ ዲላ፣ ጂንካ እና ሌሎች የደም ባንኮችም አገልግሎት የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ በርካታ ወጪዎችን ይቀንሳል።
በመሆኑም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ የዎላይታ ሕዝብ ተወካዮች፣ ሲቪክ ማህበራት እና ታዋቂ ግለሰቦች ዎላይታ በክልሉ መቀመጫነቷ የሚገባትን መልካም ዕድል በፖለቲካዊ ሽኩቻ ወደ አርባ ምንጭ እንዲሄድ መፍቀድ እንደሌለባቸው WT ሚዲያ ያሳስባል።
የአከባቢው የሕክምና አገልግሎት አስተዋፅኦ
በተለይ እጅግ በርካታ የደም ሕክምና አገልግሎት በመስጠት የሚታወቁትና በኢትዮጵያ ደረጃ የመጀመሪያው የአጥንት ቀዶ ጥገና ማዕከል የሆነው ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል፣ አንጋፋውና በደቡብ ኢትዮጵያ ብቸኛው የኩላሊት እጥበት ማዕከል (Dialysis centre)፣ እንዲሁም በዓመት 25000 ዩኒት ደም ለታካሚዎች በመስጠት ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቀጥሎ በኢትዮጵያ ሁለተኛ የሆነው የዎላይታ ሶዶ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ይገኛሉ።
በተጨማሪም ለ14 ሆስፒታሎች የደም አገልግሎት እየሰጠ ያለው የዎላይታ ሶዶ ደም ባንክ እያለ፣ ማሽኑን ወደ አርባ ምንጭ መላኩ “ትልቅ የሞራል ውድቀት” ነው ሲል WT ሚዲያ ከደረሰው መረጃ መረዳት ይቻላል።
ከዚሁ ከፖለቲካ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው የጤና ጉዳይ ላይ ጭምር ርዕሰ መስተዳድሩ ያሳዩት አድሏዊነት በተጨማሪ በፌዴራል መንግስት በጀት አማካኝነት በራሳቸው የትውልድ አካባቢያቸው ብቻ በርካታ ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን በማስገንባት ላይ መሆናቸው ክልሉ 32 ብሄረሰቦችን ያቀፈ ቢሆንም፣ የልማት ትኩረቱ በአንድ አካባቢ ላይ ማተኮሩ በሌሎች የክልሉ ከተሞች እና ብሄረሰቦች ዘንድ የመገለል ስሜት ፈጥሮ ቅሬታዎችን ማስነሳቱ ይታወቃል።