GridArt_20251212_150317249

“የጊፋታ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገብ ከባህል ዕውቅና ባሻገር የህዝቡ የፖለቲካዊ ትግልና የሥራ ቁርጠኝነትን የሚያሳይ በመሆኑ ልምድ ቀስመናል፣ ለመላው የዎላይታ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ” – ቁሕዴፓ

የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ)፣ የዎላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ጊፋታ” በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰስ ባሕላዊ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡን ተከትሎ የተሰማውን ደስታ በይፋ ገልጿል።

ፓርቲው ለ WT Media በላከው መልእክት፣ ይህ ስኬት ለሌሎችም የፍትህና የሰላም አስተዋፅኦ ለማድረግ ትምህርት መሆኑን አስገንዝቧል።

ቁሕዴፓ የዎላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ሥነ-ሥርዓት የሆነው ጊፋታ በቀን 1/4/2018 ዓ.ም. በዩኔስኮ መመዝገቡን አረጋግጧል።

ቁሕዴፓ “ከቁጫ ሕዝብ አጎራባቾችና ከቁጫ ጋር ጠንካራ ትስስር ካላቸው ብሔሮች መካከል አንዱ ዎላይታ ሲሆን የዚህ ሕዝብ ደስታ የቁጫም ሆነ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ደስታ እንደሆነ ቁሕዴፓ ያምናል” ብሏል።

ፓርቲው የጊፋታ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገብ ከባህል ዕውቅና አልፎ የፖለቲካዊ ትግልና የሥራ ቁርጠኝነትን የሚያሳይ መሆኑን ገልጿል።

“ተግቶ መሥራትና ቁርጠኝነት በዓለም ለመታወቅና ለዓለም ሰላምና ፍትሕ አስተዋጽኦ አበርካች ለመሆን እንደሚያበቃ ከጊፋታ በዩኔስኮ የመመዝገብ ስኬት ፓርቲያችን ትምህርት ወስዷል” በማለት፣ ለህዝብ ለህዝብ ትስስር ተገቢውን ትኩረት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በመጨረሻም ቁሕዴፓ “ለመላው የዎላይታ ብሔር አባላት፣ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ እንኳን ደስ አላችሁ!” የሚል የደስታ መልእክት አስተላልፏል።

🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏

Voice of Marginalized Community – WT Media