ኢትዮጵያ ነፃ አውጥታናለች። … !
“እኔ እዚህ የተገኘሁት ንግግር ለማድረግ አይደለም። ይልቅ የኢትዮጵያን ሕዝብና ወንድሜን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ነው።
ኢትዮጵያ ለእኛ እናታችን ናት። ያለኢትዮጵያ ድጋፍ እኛ አሁን የደረስንበት አንደርስም ነበር። ቀዳማዊ አጼ ኃ/ሥላሴ የመጀመሪያው እኛን ከሰሜን ሱዳን ጋር ሰላም እንዲፈጠር ጥረት ያደረጉ ናቸው።
ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም፣ ጠቅላይ ሚንስትር መለስና ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ድጋፋቸውን አልነፈጉንም።”
ኢትዮጵያ ማለት እናታችን ናት። … እናታችን ነፃ አውጥታናለች። … “
የደቡብ ሱዳኑ #ሳልቫኬር ማዮርዲት
ውድ ኢትዮጵያውያን ሆይ እኛ በኡጋንዳ ውስጥ በብሄር ክፍፍል ብዙ ተሰቃይተናል፡፡
እኔ ከዚህ ዘር ነኝ፣ አንተ ከዚህ ዘር ነህ የሚለው ነገር ክፉኛ ጎድቶናል፡፡ እናንተ ኢትዮጵያውያንም ከዚህ ከኛ ጉዳት ልትማሩ ይገባል፡፡”
የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት #ዩዌሪ ሙሰቨኒ“ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃነት እናት ናት። … ኢትዮጵያ እናታችን ናት። እናት ሰላም ካልሆነች ማንም ሰላም አይሆንም”
“የአፍሪካ እናት ኢትዮጵያ ሰላም ሳይኖራት ምስራቅ አፍሪካም መላው አፍሪካም ሰላም አይሆንም። ወንድሜ ዐቢይ ከፊትህ ብዙ ስራ ይጠብቅሃል፡ በርትተን ቀጠናችንን የዕድገትና የትብብር ማዕከል እናደርገዋለን።”
የኬንያ ፕሬዚዳንት #ኡሁሩ ኬንያታ
የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሃገር አንድነት፣ ለእድገት እና ለሰላም በጋራ እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሙሃሙድ እንዳሉትም ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትን እና ምርጫ ያንጸባረቀ ነው፡፡
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት #ሙሃሙድ ኡቡሃሪ
በዚህ ልዩ በሆነ ቀን እዚህ በመገኘቴ ክብር ይሰማኛል፤ በዚህም ለወንድሜ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ ።
አያይዘውም ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት ያበረከተችውን እና ያላትን ድጋፍ እና ክብር አድንቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካን እንቅስቃሴ መስራችና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ናት ብለዋል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ብዙ ችግሮች ቢያጋጥሟትም የሚገጥማትን ፈተና ሁሉ በራሷ መንገድ ትፈታቸዋለች ፡፡ አሁንም ጠንካራ ሀገር ሆና ቀጥላለች ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ ለዘለዓለምም ትኑርም ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
የጅቡቲው ፕሬዚደንት #ኢስማኤል ኡመርጌሌህ
