የትምህርት ሚኒስቴርና የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በያዝነዉ በጀት አመት በዎላይታ ዞን በሚገኙ የተለያዩ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚካሄደዉን የመማር ማስተማር ሂደት ለመደገፍ አቅዶ ከሚሰራቸዉ ስራዎች አንዱ የሆነዉ ይህ የቁሳቁስ ድጋፍ ነዉ ተብሏል፡፡

የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በሃገሪቱ ደረጃ የላቀ ዉጤት የሚያስመዘግቡ እና ከሀገር ዉጪም ድረስ ተወዳዳሪ የሆነ ትዉልድን የሚያፈራ ግንባር ቀደም ትምህርት ቤት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ የበለጠ እንዲሰራ ደግሞ በየጊዜዉ የሚደረግ ድጋፍ መቀጠል ያለበት በመሆኑ ለቀጣይ ጊዜም እንደዚህ አይነት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የተነገረዉ፡፡

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለትምህርት ቤቶች በድጋፍ መልክ የተሰጡ ቁሳቁሶችም በገንዘብ ሲተመን ብር ዘጠኝ መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት የሚገመት ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲም በበኩሉ በዎላይታ ልማት ማህበር ሊቃ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ተማሪዎችም የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ብር ዘጠና ሁለት ሺህ ብር የሚያወጣ እንደሆነ ልማት ማህበሩ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት የመማር ፍላጎትና ችሎታ እያላቸዉ በወላጆቻቸዉ የኢኮኖሚ አቅም ማነስ ምክንያት የመማር እድሉን ላላገኙ ተማሪዎች የሚያደርገዉን ድጋፍ በመረዳት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱንና የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን ለተደረገላቸዉ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *