በዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ለአጠቃላይ ፐብሊክ ሰርቫንት በመጀመሪያ ዙር ሲሰጥ የነበረው የብልፅግና ፓርቲ ሥልጠና ተጠናቅቋል፡፡
ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያ ዙር ፐብሊክ ሰርቫንት ብልፅግና ፓርቲ ስልጠና በፓርቲ ታርክ በኢትዮጽያ ፖለቲካ፣ የፓርቲው መሠረታዊ ዕሳቤዎች፣ የሚገጥሙ መሰናክሎች፣ ቀጣይ አቅጣጫዎች፣ ወቅታዊ ጉዳዮች መሻገሪያ ትልሞችና
በተያያዙ ጉዳዮች ሥልጠናና ውይይት ሲደረገው ቆይቶ ዛሬ ማጠቃላያ አገኝቷል፡፡
በሥልጠናው ፓርቲው የለውጥ ጉዞን ከጀመረበት ማግስት አንስቶ የተሠሩ ፣ የተከሰቱና የተቀመጡ አቅጣጫዎች፣ እንዲሁም ለውጡ ያመጣቸው በየቦታው የሚነሱ ጥያቄዎችና ችግሮችን
በመፍታት ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ውይይት ሲደረግበት ቆይቷል፡፡
የተጀመሩ በርካታ ተግባራትን በማስቀጠል ሁሉም በአንድነት የሚበልፀግበትን ኢትዮጽያ ለማየት ሁሉም ሊተጋ እንደሚገባ በተቀመጠው ማጠቃለያ ስምምነት ተደርሶበት ሥልጠናው ተጠናቅቋል፡፡
ከቀጣይ ሣምንት ጀምሮ በሁለተኛ ዙር ሥልጠና የሚቀጥል ሲሆን በመጀመሪያ ዘር ያልተሳተፉ ፐብሊክ ሰርቫንት ተሳታፊ እንደሚሆኑም ማወቅ ተችሏል ሲል የከተማው ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ዘግቧል ፡፡


