በዎላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በብልሹ አሰራር የተጠረጠሩ አመራሮችና ግለሰቦች በቁጥጥር እየዋሉ መሆኑ ተገለፀ

በቦዲቲ ከተማ በከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ በአመራርነት፣ በባለሙያነት እንዲሁም ተዛማጅ መስሪያቤት ስራዎች የተሰማሩ ግለሰቦች በብልሹ አሠራር ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ ከስፍራው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በአሁኑ ወቅት ከተማዋ አቃቤ ህግ ጉዳዩን በዝርዝር ምርመራ ለማካሄድ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች በተጨማሪ የተለያዩ አመራሮችና ሠራተኞችን በህግ ቁጥጥር ስር ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩም ተገልጿል።

ከተማ አስተዳደሩ በየትኛውም ስራ ውስጥ ሆነው በብልሹ አካሄድ ውስጥ የገቡ ግለሰቦች ላይ ከመቸውም ጊዜ በላይ ተከታትሎ ወደ ህግ የማቅረብ ስራና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ሙሉ የምርመራ ህዴት ስያልቅ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዝርዝር መረጃዎችን ተከታትለን እናቀርባለን።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡Wolaita Timese/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw…
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

#WolaitaTimes, 07/02/14 E.C , Sodo, #Ethiopia