በደቡብ ክልል የኮንሶ ዞን አስተዳደር በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በበልግ ዝናብ መዘገየት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች የእንሰሳት መኖ ሳር ድጋፍ አደረገ

የኮንሶ ዞን አስተዳደር በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በበልግ ዝናብ መዘገየት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ
የኮንሶ ዞን አስተዳደር በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በበልግ ዝናብ መዘገየት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የበልግ ዝናብ እጥረት ባስከተለው ችግር ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በቦረና ህዝብ ላይ የደረሰው ጉዳት የእኛም ጉዳት ነው ብለዋል።

እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለጻ 18 የጭነት መኪና የእንሰሳት መኖ እና ሁለት ቦቲ ውሃ በድርቅ ለተጎዱ እንሰሳት ድጋፍ አድርገዋል።

የኦሮሞ እና የኮንሶ ህዝቦች አንድ ናቸው ያሉት አቶ ዳዊት አስደንጋጭ የሆነውን የእንሰሳትን ሞት ለማስቀረት የበኩላችንን ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉም ጠቁመዋል።

በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱራሀማን አብደላ እንደተናገሩት ለቦረና ወንድም ህዝቦቹ ድጋፍ በማድረግ ረገድ ኮንሶ ዞን የመጀመሪያ በመሆኑ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘገባ እንደሚያመለክተው የቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጃርሶ ቦሩ ተደረገላቸው የእንሰሳት መኖና ውሃ ድጋፍ በቦረና ህዝብ ስም አመስግነዋል።

እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለጻ ለችግራችን ደርሳችሁ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረጋችሁ ንድማማች ህዝቦች መሆናችሁን በፍቅር አሳይታችሁናልና ሲሉም ተናግረዋል።