የተሾሙ አመራሮች በመደጋገፍ በመቀናጀትና አንድነትን በመፍጠር ለአከባቢው ለውጥ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንዳለባቸው የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ አሳሰቡ
ዋና አሰተዳደሪው በዞኑ ውስጥ በተለያዩ መዋቅር ለተሾሙት ጥሪያቸውን አስተላልፏል።
በዳሞት ወይዴ ወረዳ ምክር ቤት ባካሄደው ማጠቃለያ መድረክ ላይ የዎላይታ ዞን ዋና አሰተዳደር አቶ አክልሉ ለማ ተገኝተው አዲስ ለተሾሙት አመራሮችና የምክር ቤት አባላት መልዕክት አስተላልፏል።
በዞኑ በተለያዩ ደረጃ ሹመት የተሰጣቸው አመራሮች ህብረተሰቡን በቅንነት ፣ በታማኝነትና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ማገልገል እንዳለባቸው ጥሪ አቅርቧል።
የምክር ቤቱ አባላት ህዝብን ለማገልገል የተሾሙ አመራሮችን በመደገፍ ፣ በመተቸት እንዲሁም ከጎናቸው በመቆም ለብልፅግና የሚደረገውን ጉዞ መደገፍ እንዳለባቸው አሳስቧል።
የተሾሙ አመራሮች በመደጋገፍ ፣ በመቀናጀትና አንድነትን በመፍጠር ለወረዳው ለውጥ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንዳለባቸው አጥብቀው አሳስቧል።
የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አሰተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ አዲስ የተሾሙ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው አሳስቧል።
