የጌዴኦ ዞን በቅርቡ የመንግሥት ምስረታ በማድረግ አዳዲስ አስተባባሪ አካላት ማዋቀሩ የሚታወስ ሲሆን አዳዲሱ የዞኑ አስተባባሪ አካላትም ከዩኒቨርሲቲ አመራር ጋር ትውውቅና በቀጣይ ስራች ዙሪያ በጥልቀት ተወያይቷል።

በውይይቱ ወቅት ዩኒቨርስቲው ከዞኑ ጋር በጋራ በሚያከናውናቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ተወያይቷል።

ዩኒቨርሲቲው ለማህበረሰቡ በሚሰጠው አገልግሎትና እያከናወነ ያሉትን ዋና ዋና ስራዎች  ላይ በመወያየት በቀጣይ እስከታችኛው ማህበረሰብ ተደራሽ በሚሆኑ ስራዎችን በጥልቀት የማቀድ፣ ለተግባራዊነታቸውም ክትትልና ድጋፍ በማድረግ፣በመጎብኘት እንድሁም ያሉትን ክፍተቶች በማረም በጋራ ተቀናጅተው ለመስራት አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን የዞኑ የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያደረሰው መረጃ ያመለክታል።