
ዋና አስተዳዳሪው ከፅህፈት ሰራተኞች ጋር ተወያዩ
የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ከጽ/ቤታቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ትውውቅ በማድረግ በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ተወያዩ።
ዋና አስተዳዳሪው በትውውቃቸው ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በጽ/ቤቱ ብሎም በሌሎች መስሪያ ቤቶች ያለ ባለሙያ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጥንካረ በመሻገር ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
መስክ ወጥተው ለሚሰሩ ባለሙያዎች የሚያስፈልጋቸው ሎጂስቲክስ እንዲሟላ በትኩረት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።
ሁሉም ባለሙያዎች ለማህበረሰቡ የሚፈለገውን አገልግሎት በቅንነትና በመልካም ስነ ምግባር በማገልገል የተገልጋይ እርካታን ከፍ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
እንደ ዞኑ መኮጉ ዘገባ የጽ/ቤቱ ሰራተኞች በመስሪያ ቤት ስራ ብቻ ሳይሆን በሚኖሩበት አካባቢ ሁሉ ከጓሮ አትክልት ጀምሮ በማምረትና ሌሎችም እንዲያመርቱ አርአያ በመሆን ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
ከጽ/ቤቱ ሰራተኞች ከፋይናንስ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ በግዥና በውሎ አበል አከፋፈል የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።
