አሸባሪው የህወሀት ቡድን የከፈተውን ሀገር የማፍረስ ተግባር ለመመከት በጋራ መቆም ይገባል – በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች

መንግስት ያስተላለፈውን ሀገር የማዳን ጥሪ ከወጣት እስከ አዋቂ በመቀበል ጥቃቱን መቀልበስ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

መንግስት እያካሄደ ያለውን ዘመቻ የዞኑ ነዋሪዎች ሲደግፉ መቆየታቸውን ገልፀው በተለይ ወጣቱ አሁን የተላለፈውን ሀገር የማዳን ጥሪ ተቀብሎ በሀገራዊ አንድነት እንዲነሳ ጠይቀዋል።

ወራሪው ቡድን አሁን ላይ ያለ የሌለ ሀይሉን አስተባብሮ ጥቃት ለማድረስ እየሞከረ ቢሆንም በኢትዮጵያዊ ህብር ሁሉም ይቀለበሳል ብለዋል።

መንግስት እያደረገ ያለውን ሀገር የማዳን ዘመቻ አጠናክሮ እልባት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመተባበር የጋራ ጠላት የሆነውን አሸባሪ ቡድን ማስወገድ ይኖርበታልም ተብሏል።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 22/02/14 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹