የፌደራል #የሥነምግባር እና #የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በኮሚሽኑ የ100 ቀናት ዕቅድ ላይ ለመወያየት ለሰራተኞች በተዘጋጀው መድረክ ላይ ገልጸዋል፡፡

ለኮሚሽኑ ሰራተኞች በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንደተገለፀው በሚቀጥሉት 100 ቀናት ውስጥ ተቋማዊ አቅምን የመገንባትና የማሳደግ፣ የሥነምግባር ግንባታን የማጠናከር፣ #የሙስና መከላከል አቅምን የማሳደግ፣ ሙስናና ብልሹ አሰራር ነክ የሆኑ መረጃዎችን የመለየትና የመተንተን ጥራትን የማሳደግ እና አሰራሮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የማስደገፍ ሥራዎች ይሰራል፡፡

ኮሚሽኑ ቀደም ሲል ያልሰራቸው አዳዲስ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራዎች እንደሚሰሩም በውይይቱ ላይ ተጠቅሷል ሲል ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ 

ከ100 ቀናት ዕቅድ በተጨማሪ የኮሚሽኑ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሰራተኞቹ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 25/02/14 E.C , Sodo, Ethiopia