“አሸባሪው ህወሓት በሀሳብ ልዩነት ማሸነፍና በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር ሲያቅተው ወደ ጦርነት ገብቷል” ሲሉ አለም አቀፉ የፖለቲካ ተመራማሪ ሮናልድ ማርሻል አመለከቱ።
በፍራንስ 24 ‘ዘ ዲቤት’ መርሐግብር ላይ የተሳተፉት በፈረንሳይ የሳይንሳዊ ምርምር ማዕከል አንጋፋ ተመራማሪ ሮናልድ ማርሻል “በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በግርድፉ ከመዳሰሳችን አስቀድሞ በሸባሪው ህወሓት ሲመራ የነበረውን መንግስት ማወቅ ይገባናል” ብለዋል።
በሽብር ቡድኑ ለዘመናት የቆየው አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝቦች ተቀባይነት ማጣቱን ተከትሎ ለውጥ መምጣቱን አውስተው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን በመጡበት ጊዜ የከፉ ችግሮች የተፈጠሩበትና ብዙሃን የተፈናቀሉበት ወቅት ነበር በማለት አስታውሰዋል።
በህዝቦች የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል እና ህወሃትን ለህግ ተገዢ ለማድረግ መንግስት መስራቱን አመልክተው፤ “ሂደቱ ሁሉም እኩል የሚስተናገድባት ኢትዮጵያን ለመገንባት እንቅስቃሴ የተጀመረበት በመሆኑ ችግሮች ተፈጥረዋል” ብለዋል።
“በአንጻሩ አሸባሪው ህወሓት ከአመታት በፊት ያጣውን ስልጣን ለመመለስ አዲስ አበባን እንቆጣጣራለን በማለት ተንቀሳቅሷል” ሲሉ አስገንዝበዋል።
የአገሪቱን ልዩነቶች ለመፍታት የኢትዮጵያ ህዝብ በኢትዮጵያዊነት መርህ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተናግረው፤ ነገር ግን የተለየ ሃሳብ መስማት የማይፈልጉ አንዳንድ አካላት ወደ ጦርነት መግባታቸውን ገልጸዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ “አሸባሪው ህወሃትም በሀሳብ ልዩነት ማሸነፍና በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር ሲያቅተው ወደ ጦርነት ገብቷል” ብለዋል።
በሌሎች አገራት የታየው አስከፊ ነገር እንዳይከሰት ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መንቀሳቀስ እንደሚገባም ነው ተማራማሪው አመላክቷል።