የጌዴኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ከፀጥታና ባለድርሻ አካላት ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይና የሃገር ህልውና ለማስጠበቅ በወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር ዙሪ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

የአካባቢያችን ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ የፀጥታ አካላት እያደረጉ ያሉ እንቅስቃሴ አጠናክሮ ለማስቀጠልና ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር ከመቼዉም ጊዜ በላይ ሥራ ለመስራት መዘጋጀታቸውን የውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል።

ሰላም ለሁሉም ወሳኝና አስፈላጊ በመሆኑ  ሰላም ለማደፍረስ ሰርጎ የሚገቡትና ተላላኪዎች የጁንታ ሽብር ቡድን በማጠን ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ሁሉም አከባቢውን መጠበቅ እንዳለበት ተገልጿል።

ኢትዮጵያን ከችግር ሊያወጣ የሚችል ሁሉን አቀፍ አሰላለፍ በማድረግና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሚናዉን እንዲወጣ ተጠይቋል።

የጌዴኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አበባየሁ ኢሳያስ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በመረዳት የአከባቢያችንን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ መረጋገጥ የፀጥታ መዋቅሩን ዝግጁ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጿል።

አክለውም ማህበረሰቡ ለፀጥታ መዋቅሩ አጋዥ በመሆን ሰርጎ ገቦችን በመከለካልና በየትኛውም ጊዜ በቅንጅት ለሰላም ዘብ በመቆም የህግ የበላይነትን ለማስከበር ዝግጁ መሆን እንዳለበትም በአጽንኦት ተናግረዋል።

በመድረኩ የሃገር ህልውና ለማስጠበቅ በወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አካል አስፈጻሚ አካላት ህጋዊ እርምጃ መውሰድ የሚገባቸው ስለመሆኑ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል መባሉን ከስፍራው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የተላከው መረጃ ያመለክታል።