የዳሞታ ዎላይታ ገበሬዎች ኅብረት ስራ ዩኒየን የ2013 ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2014 ምርት ዘመን ከአባል ኅብረት ስራ ማህበራት ጋር የግብርና ምርት ግብይት ትስስር የምክክር መድረክ በዎላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል፡፡
ዩኒየኑ በ2014 በጀት ዓመት በቡና ግብይት ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ በላይ የውጭ ሚኒዛሬ ለማግኘት አቅዶ እየሰራ መሆኑን የዩኒየኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳሳና ዋና ገለጹ፡፡
የዎላይታ ዞን ኅብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል የዳሞታ ወላይታ ኅብረት ስራ ዩኒየን እስካሁን በሰራቸው ስራዎች በረካታ የዞኑ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ዩኒየኑ ከተቋቋመበት ረዥም ጊዜ አንጻር በአባላት ቁጥርና በካፕታል መጠን ብዙ ማደግ ሲገባው እስካሁን ድረስ 76 ሸረታ ማህበራት እና ከ25 ሺህ አባላት ብቻ መሆናቸውን እንደ ድክመት የሚገለጽ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ቀጣይ የዞኑ ኅብረት ስራ ጽ/ቤት ዩኒዩኑ ውጤታማ እንዲሆንና የአባላቱ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ወ/ሮ ሰላማዊት አረጋግጠዋል፡፡
የዳሞታ ዎላይታ ገበሬዎች ኅብረት ስራ ዩኒየኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳሳና ዋና ዩኒየኑ የግብይት ስርዓቱን ፍትሃዊ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ የቆየ ቢሆንም ከዕድሜው አንጋፋነት አንጻር ሲታይ የሚፈለገውን ያህል ውጤት አስመዝግቧል ማለት አይቻልም ብለዋል፡፡
የዎላይታ ቡና ከዚህ በፊት የሲዳማ ሲ በሚል ስም ሲላክ እንደነበረ ያስታወሱት አቶ ዳሰነ አሁን የወላይታ ቡና በራሱ ስም ለውጭ ገበያ የሚቀርብበትን ዕድል ስላገኘ የግይት መጠኑን ከፍ ለማድረግ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡
9 ኮንታይነር ቡና ለጀርመንና ለፈረንሳይ ሀገራት ተልኮ 1 ሚለዮን 6 መቶ ሺህ ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ዩኒየኑ በ2014 በጀት ዓመት በቡና ግብይት ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ በላይ የውጭ ሚኒዛሬ ለማግኘት ትኩረት ሰጥቶ እሰታ ነው ብለዋል፡፡
የዩኒየኑን ካፒታል ለማሳደግ ከውስጥና ከውጭበሚገኙ ገቢዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አቶ ዳሳና ተናግረዋል፡፡
ከወለድ ነጻ ብድር ለማግኘት በሚደረገው ጥረት የወላይታ ዞን አስዳደርን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ታምኖ እየተሰራ መሆኑን ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል።
የአባላት ቁጥርን በመጨመርና ነባር አባላት የዕጣ ቁጥርን በዛ አድርገው እንዲገዙ በማድረግ የውስጥ ገቢ አቅምን ለመጨመር ትኩረት ተሠጥቶ እንደሚሰራና በቅርቡ የአባላትን ቁጥር ከ40 ሺህ በላይ ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ የተሳተፉ የመሠረታዊ ኅብረት ስራ ማህበር አባላት እንዳሉት የምርት ጥራትን በማሳደግ ራሳቸውንና ማህበራቸውን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 26/02/14 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹