የዲላ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ መድኃኒት ግርማ የወለዱትን አራት ሎጆቻቸዉን፤ ወ/ሮ አስናቀች ዳምጠዉ ሁለት ልጆቻቸዉን ምንም ብሆን ከሃገር የሚበልጥ ጉዳይ የለም በማለት በአሸባሪዉ አረመኔ ቡዱን በሃገር የተደቀነዉን ሃገርን የማፍረስ ሴራ እንድመክቱ ወደ ጦር ግንባር የላኩት ጀግኖች እናቶች ናቸዉ፡፡

ወ/ሮ መድኃኒት ልጆቻችን እምዬ ኢትዮጲያ ከዉስጥና ከዉጭ ወራሪ ኃይል ለመታደግ ስለ ሄዱ ማዘን አያስፈልግም ብለዋል፤ በሌላ በኩልም ወ/ሮ አስናቀች ጀግንኘታቸዉን በፉከራ ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ይህንን የተናገሩት በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ በተካሄደዉ የሃገር መከላከያ ሰራዊት በምደግፍና የአሸባሪዉ ህወሓትና የሸኔ ቡዱኖች ሃገርን የማፈረስ ሴራ የምያወገወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ ላይ ነዉ፡፡

የመርሃ ግብር የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዲላ ከተማ ከንቲባ አቶ ተስፋጽዮን ዳካ እንደተናገሩት የሸባሪ ባንዳዎች በየ አከባባችን መኖራቸዉን በመገንዘብ ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም በሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የደረሰዉን ጥቃት ታርክ የማይረሳና ለሃገራቸዉ ስሉ ህይወታቸዉን ለተሰዉት ጀግኖቻችን መከላከያ ሰራዊት ታላቅ አክብሮት አለን ብለዋል፡፡

የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዮት ደምሴ በበኩላቸዉ በሃገር ሉዓላዊነት ለተጋረጠዉ አደጋ የበኩላቸዉን ለመወጣት ከመቸም በላይ ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

መላዉ የሃገራና የዞን ህዝቦች ከመቸም በላይ የአከባቢዉን ሰላም ተግተዉ በመጠበቅና ለጸጥታ ዝጋት የሚሆኑት ጉዳዮች በምታዩበት ጊዜ ለሚመለከተዉ ለጸጥታ አካላት ጥቆማ በማድረግ ሃገርን እንድታስቀጥሉ ስሉ አስተዳዳሪው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ልጆቻቸዉን ወደ መከላከያ ሰራዊት ለላኩት የዲላ ከተማ ነዋሪ እናቶች የከተማ አስተዳደር፤ የዞን መንግስትና የሐይማኖት ተቋማት ድጋፍ እንሚያደርግላቸዉ ገልጸዋል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ያለምንም ጸጥታ ችግር የተጠናቀቀ ስሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የዲላ ከተማና የዲላ ዙሪያ ነዋሪዎች፤ የተለያዩ ተቋማት፤ ተፎካካር ፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የሐይማኖት አባቶች፤ አባጋዳዎች፤ የሃገር ሽማግለዎች፤ የጽጥታ ኃይሎች፤ የሚዳያ ተቋማት እና የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍል ተሳትፈዋል፡፡