አሸባሪዎቹን ህወሃት እና ሸኔን የሚያወግዝ እና የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በሰልፉ ላይ የታደሙ ነዋሪዎችም የተለያዩ መፈክሮችን ይዘው የወጡ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ፤ “የድላችን ሚስጥር ፍትህ ፣ሀቅና እውነት ናቸው፤ ለውጭ ጫና የሚበረከክ ማንንት የለንም፤ የአብሮነት ጉዟችን በሽብርተኞች አይደናቀፍም፤ በመራር ትግል ጣፋጭ ድልን እንቀዳጃለን” የሚሉ ተጠቃሽ ናቸው።

በተጨማሪም አንዳንድ ዓለም አቀፍ መጋናኛ ብዙሃን እና የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እንዲያቆሙ የሚጠይቁ መልክቶችም ተንፀባርቋል።