በዎላይታ ሶዶ ከተማ እንያት ሆስፒታል ከሁለት ሳምንታት በሁዋላ ሙሉ ዝግጁቱን አጠናቆ በተደራጀ መንገድ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለው በሆስፒታሉ የተለያዩ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር የስራ ማስታውቂያ አውጥቷል።

ከታች በማስታወቂያ በተገለፀው መነሻ በሁሉም የህክምና ዘርፍ የሰለጠናችሁ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች በድርጅቱ ለመስራት ፍላጎት ያላችሁ ባለሞያዎች ከህዳር 2/2014 እስከ ህዳር 6/2014 ዓ.ም ድረስ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከሲቪ ጋር በማያያዝ በሆስፒታላችን የሰው ሀብት በአካል በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን የሆስፒታሉ አስተዳደር ያሳውቃል!

በዎላይታ ሶዶ ላለፉት አስራ ሶስት ዓመታት ዘመናዊ ህክምናን በማስተዋወቅና በመስጠት የሚታወቀው እንያት ክሊኒክ ማስፋፊያ አካል የሆነው ይህ እንያት ሆስፒታል እጅግ በተራቀቁ ዘመናዊ መሳርያዎችንና ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች አደራጅቶ ወደ ስራ በሚገባበት ጊዜ በከተማው በዞኑ እንዲሁም አጎራባች አከባቢዮች ላይ ተመራጭና አማራጭ የህክምና ማዕከል በመሆን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊኖሩ የሚችሉ የታካሚ ሪፈራልን ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት የሚያስችል የህክምና ተቋም እንዲሆን የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩም ተነግሯል!!

እንያት ሆስፒታል

አድራሻ ⏩ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ከብሩህ ተስፋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፊትለፊት ያገኛሉ⏬ ስልክ ቁጥር ⏬
0465512916
0913469148

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: