በኦሞ ማይክሮ ፋይናስ ተቋሞ የዎላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ያይና እንዳሉት ተቋሙ በክልል ደረጃ በቁጠባ አስባሰብ የተሸለ ውጤት በማስመዝገቡ 2ኛ መውጣቱን ተናግረዋል፡፡
በ2012 በጀት ዓመት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች 1 ቢሊየን 31 ሚሊየን ብር ቁጠባ መሰባሰባቸውን ገልፀዋል፡፡
ለሴቶች፣ ለወጣቶችና ለአርሶ አደሮች 459 ሚሊየን ብር ብድር ማሰራጨት መቻሉን አቶ ተመስገን ጠቁመዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ 359 ሚሊየን ብር ማስመለስ እንደተቻለም አስታውቀዋል፡፡
ዲስትሪክቱ የላብቶፕ፣ የኮምፒውተርና የቢሮ ቁሳቁስ ተሸላሚ ሲሆን በክልሉ ከሚገኙ 223 ቅርንጫፎች የዱጉና ፋንጎ ወረዳ ሜዳሊያና ዋንጫ ተሸላሚ መሆኑን አቶ ተመስገን ተናግረዋል፡፡
ለስኬቱ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የተቋሙን ሰራተኞችን እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል፡፡
ሽልማቱ የ2013 በጀት ዓመት ውጤት እንዲሳካ የሚያበረታታ መሆኑን ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን መመሪያ ዘግቧል፡፡

