የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከከተማው ንግዱ ማህበረሰብ ጋር በሀገራዊና አካባቢያዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል።
በምክክር መድረኩም የነጋዴ ማህበረሰብ የአሁናዊ ሀገራዊና አካባቢያዊ ወቅታዊ ጉዳዮች በንቃት በመገንዘብ ነጋዴ ማህበረሰብ ለሀገር ሠላም ዘብ ይቁም ፣ አከባቢይና ሀብታቸውንም ይጠብቁ ለዚህም ከመንግስት ጎን እንዲሆኑም የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መርክኔ ማለዳ ጥሪ አቅርበዋል ።
አቶ መርክኔ አክለውም ከዚህ በፊትም ከከተማችን ንግዱ ማህበረሰብ ጋር በሠራናቸዉ ሥራዎች ሁሌም ዉጤታማ ነን በማለት በማመስገን አሁንም በሶስት ዋና ወና ጉዳዮች ትኩረት እንሰጣለን ብለዋል ።
እነዚህም የአከባቢውና የራሳቸውን ደህንነት መጠበቅ ፣ ለሀገር በየጫካው የሚዋደቁ ጀግና መከላከያ ሠራዊትን መደገፍና ከመንግስት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ናቸው በማለትም ለዚህም የነጋዴው ማህበረሰብ በቁርጠኝነት ሊነሱ ይገባል ብለዋል ።
አቶ መርክኔ ለተሳታፊዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያዎችን መጠበቅ እንዳለባቸው ጠይቀው ለዚህ ተግባር ከተሠማሩ አካላትም ጋር እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርበዋል ።
አቶ መስፍን ቶማስ የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ እንደተናገሩት ሀገር የማፈራረስ እኩይ ተግባር ይዞ የተነሳው ጠላትን መክተን ወደ ልማት ለመዞር ጊዜ ሊወስድ አይገባም፣ ፈጥነን ወደ ሥራ ገብተን በዛዉ ፍጥነት እየተወጣን ነዉ ብለዉ ለዚህም ህዝባዊ አደረጃጀቶችን አጠናክረን አካባቢያችን እየጠበቅን ጀግናውን መከላከያ ሠራዊት እንደግፋለን ብለዋል ።
ከዚህ በፊትም የከተማችን ነጋዴ ማህበረሰብ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋቸውን ያመሰገኑት አቶ መስፍን ይሄ ድጋፍ ደግሞ በፍጥነት ጠላትን ለመመከት የሚዉል ነዉ ብለዋል ።
ንግዱ ማህበረሰብም በሰጡት አስተያየት ነጋዴ በባህር በአንድ አከባቢ ብቻ የሚታጠር አይደለም ፣ በዚህም አያተርፍም ሀገርን ዞሮ ይሠራል ብለዉ ለዚህም የሀገር ሠላም ወሳኝ በመሆኑ ለሀገር የማንከፍለዉ መስዋዕት የለም ብለዋል ።
እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈልም መዘጋጀታቸውን ገልፀው የአካባቢያችን ሠላምም እንጨብቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን መምሪያም እንጠብቅ ብለዋል ።
በመድረኩ የድጋፍ ሥራዉን የሚያስተባብር ከመንግስት መዋቅርና ከነጋዴዎች የተሰየመ ሲሆን ወደ ተግባርም ከአሁኑ እንደሚገቡም ተረጋግጧል።