የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዙሩ ካደረጋቸው 4 ጨዋታዎች ሁሉንም በአሸናፊነት በማጠናቀቅ 12 ነጥብ በመያዝ 12 ነጥብ ካለው ዩጋንዳ አቻው ጋር የመጨረሻውን የዋንጫ ጨዋታ በዛሬው ዕለት ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ባደረገው ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነ ።
በዩጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ሀገራት ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድኖች ውድድር
በስድስት ሀገራት መካከል በዙር ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ጥቅምት 30/2014 በተደረጉ ሦስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ተጠናቀቀ።
በውድድሩ ኢትዮጵያ ሻምፒዮን በመሆን የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ስትሆን ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ በቅደም ተከተሉ መሠረት የብርና የንሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።
