የ21 ዓመት ወጣት በዎላይታ የሰራው አነስተኛ ሄሎኮፕተር የሙከራ በረራ ተራዘመ
በዎላይታ አረካ ከተማ ወጣት ቢኒያም ብርሃኑ የተባለ የ21 አመት ወጣት ከተለያዩ ዕቃዎች በመገጣጠም አነስተኛ ሄሎኮፕቴር የሰራውን በዛሬው ዕለት በከተማዋ ወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ላይ የሙከራ በረራ ለማድረግ ቢታቀድም እንዲሁም የሙከራ በረራ ለመመልከት የመጡ በርካታ ስዎች የተገኙ ቢሆንም የዘርፉ ባለሙያዎች ስለሌሉ አደጋ ልያደርስ ይችላል በሚል በከተማ አስተዳደሩ ለጊዜው እንዲሰረዝ መደረጉን ለWT ከስፍራው የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ በፊት በዎላይታ ሶዶና አረካ ከተማ ወጣቶች ስካቫቴርና አድስ ሞዴል መኪና መስራታቸውን እናስታውሳለን።

