በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት በኩል በቦሳ ቃጫ ቀበሌ በገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ የተሰማሩ ወጣቶች በህብረት ዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ በዶሮ እርባታ በመደራጀት በቀን 400 መቶ እንቁላል በማምረት ውጤታማ መሆናቸውን ተነግሯል።
በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት በኩል የጽ/ቤቱ ክትትልና ቁጥጥር በተጠናከረ መልኩ እየተደረገ መሆኑን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ኃላፊ የሆኑት አቶ መብራቱ ተዘራ ገልጿል።
አቶ መብራቱ አክሎም ወጣቶች በማህበር በመደራጀት ከራስ ጥቅም ባለፈ ህብረተሰብንም የሚጠቅም ሥራ ነው ብለዋል።
በመቀጠልም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ቁሳቁሶችን የምክር አገልግሎቶችን እንድሁም ወጣቱ እንቁላል በማቅረብ የገበያ ትስስር በመፍጠር የተሻለ ሥራ እንድሰሩም በማበረታታት በቀጣይ እስከ 600 እንቁላል ለማሳደግ ከማህበሩ አባላት ጋር መስማማታቸው ተገልጿል።
