በዎላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በበጋ መስኖ ልማት ስራ ከ130 ሄ/ር የቆላ ስንዴ ለማልማት እየተሰራ ነው

ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የበጋ መስኖ ልማት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል።

በወረዳው በ1ኛ ዙር የበጋ መስኖ ልማት ስራ 1610ሄ/ር ማሳ ለማልማት ታቅዶ እስከዛሬ 270ሄ/ር ማሳ ለማልማት መቻሉን የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ በዛብህ ሻንካ አስታውቀዋል።

በበጋ መስኖ ልማት ስራ 130 ሄ/ር የቆላ ስንዴ ለማልማት የታቀደ መሆኑን የገለጹ ኃላፊው ከዚህም 43.5ሄ/ር ሶስተኛ ዙር የማሳ ዝግጅት መደረጉን አሳውቀዋል። ሶስተኛ ዙር የማሳ ዝግጅት ከተደረገው ማሳ ላይ 20ሄ/ር በእርሻ ሜካናይዘሽን የታረሰ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል።

የምግብ ዋስታናን ማረጋገጥ የሚንችለው አርሶ አደሩ ከዝናብ ጥገኝነት ተላቀው በመስኖ የማልማት ልምድን ስያዳብር ነው ያሉት ኃላፊው ሁሉም አርሶ አደር ያለውን የውሀ አማራጭ አሟጦ በመጠቀም መስኖ ልማት ስራ ላይ ትኩረት ልያደርግ እንደሚገባ አቶ በዛብህ ሻንካ አሳስበዋል።