የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ ነን አሉ በኦሞ ማይክሮ ፉይናንስ የዎላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ገለፀ፡፡
የዲስትሪክቱ ሴት ባለሙያዎች ለሰራዊቱ ስንቅ በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ።
በኦሞ ማይክሮ ፉይናንስ የዎላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ባለሙያ የሆኑት አስር አለቃ አለማየሁ አበራ፣ ወ/ሮ አበባ አስፋው እና ወ/ሮ ባንቺወሰን ገረመው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገራችንን ሉአላዊነት ለማስከበረ ውድ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ ጀግና ሰራዊት የትኛውንም ዋጋ ቢከፈል አይቆጨንም ብለዋል።
ከዚህ ቀደምም ሁሉም የዲስትሪክቱ ባለሙያዎች ለሰራዊቱ ከደመወዛቸው 20 ከመቶ ድጋ ማድረጋቸውን፣ አሁንም ሰንባች የምግብ አይነቶችን እያዘጋጁ መሆናቸውንና ቀጣይም አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አስር አለቃ አለማየሁ አበራ በበኩላቸው ከዚህ በፊትም ለሀገር ሉአላዊነት እስከ ግንባር ድረስ ዘምተው መመለሳቸውን ጠቁመው ሀገራችንን ነጻ ለማድረግ አሁንም ዳግም እስከ ግንባር ድረስ በመዝመት ለወዷ ሀገሬ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነኝ በማለት ተናግረዋል፡፡
አስተያየት የሰጡ ባለሙያዎች አክለውም አካባቢያቸውን በመጠበቅ፣ መከላከያን በመደገፍና አስከ ግንባር በመዝመት የሀገራችንን ሉአላዊነት እናስጠብቃለን ብለዋል፡፡
በኦሞ ማይክሮ ፉይናንስ የሶዶ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ያይና እንዳሉት ከዚህ ቀደም ከመንግስት በቀረበው ጥያቄ መሠረት የዲስትሪክና የሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ባለሙያዎች ከደመወዛቸው 20 ከመቶ ድጋፍ ማድረጋቸውንና አሁንም አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
