የከተማ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2014 አንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ላይ ድጋፋዊ ክትትል አድርጓል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አበራ አዋሾ እንዳሉት የከተማ ማዘጋጀት ቤታዊ አገልግሎቶች ፅህፈት ቤት ህገወጦችን አክርሮ በመታገል ውስን የሆነውን የህዝብ እና የመንግስት መሬት ከምዝበራ ማዳን እንደሚገባ አሳስበዋል።

የከተማውን ውበት እና አረንጓዴ ገፅታ የሚያስተጓጉል ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች መከናውን እንደሚገባም የተከበረው ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት አፅንኦት ተሰጥተዋል።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ብዙአየሁ ወልዴ ህግ እና መመሪያዎች ተከትሎ በመስራት ህገ- ወጥነት ለመከላከል የተከበረው ምክር ቤት እገዛ እንዳይለይ ጠይቀዋል።

እንደ ከተማው ኮሙኒኬሽን ዘገባ በህገወጥ ግንባታዎችን ለማፍረስ ፣ የመሬት ደላሎችን ለመቆጣጠር እና የከተማ ውበት ለመጠበቅ ማዘጋጃ ቤቱ በሙሉ አቅም በመንቀሳቀስ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰራም ኃላፊዋ ገልፀዋል።