ሀገሪቷ ከገጠማት ችግር በድል እንድትወጣ በተባበረ ክንድ ለመመከት ተዘጋጅቶ በተለያዩ መንገድ ደጀንነታቸውን እያሳዩ መሆኑንም የዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ተናግሯል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዛሬው ዕለት በከተማዋ ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ባደረገው ቆይታ በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ህወሃትና ጀሌዎቹ የሀገሪቱን ህልውና ለመፈታተን እያደረጉ የሚገኘውን እኩይ ተግባር
ኢትዮጵያ በጠላቶቿ ፊት በድል አድራጊነት የመቀጠሏ ምስጢር አንድነትንና እውነትን በመያዟ መሆኑን ተናግሯል።

በልጆቿ መስዋዕትነት ነፃነቷን አስጠብቃ የቆየች ሀገር ዛሬም በውስጥ ባንዳዎችና በአሸባሪዎች ሴራ አትፈርስም ሲሉ በከተማዋ ዞረን ያነጋገርናቸው አቶ አስራት አጌቦ እና መቶ አለቃ ቴዎድሮስ ተፈራ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን በብሔር፣ በኃይማኖትና በጎሳ በመከፋፈል ሲመዘብር የኖረውና በህዝብ የተባበረ ክንድ ከስልጣን የተወገደው ይኸው ኃይል ሀገር የማፍረስ በያዘው ተልዕኮ በአማራና አፋር ክልሎች በንጹሀን ላይ እያደረሰ የሚገኘውን ግድያና ማፈናቀል ለማስቀረት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ለሀገር ህልውና ቅድሚያ በመስጠት ግንባር ድረስ በመሄድ እያመጡ ያለው ድል አስደናቂና ጠላትን ተስፋ የሚያስቆርጥ መሆኑን አስረድተዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የሆኑት ወጣት ዮሐንስ ታንቱ እና ወታደር አየለች ግዛው ይሄንን አጥፊ ቡድን በተባበረ ክንድ ለመደምሰስ በሚደርገው ትግል ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመቆም በገንዘብ፣ በዓይነትና በሞራል እንዲሁም ተደራጅቶ አከባቢያቸውን በመጠበቅ የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥሉም የከተማ ነዋሪዎቹ አስተያየታቸውን ሰጥቷል።

በተለየም ወታደር አየለች በቁጭት ልጃቸውን ወደ ግንባር መላካቸውን ተናግረው በከተማዋ ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ከመስጠት ባለፈ አካባቢውን ከወትሮው በተለየ መንገድ ተደራጅተው እየጠበቁ መሆኑን አክለው ተናግረዋል።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከሰባት በላይ መግቢያ መውጫ ያለባት ለበርካታ ስዎች መተላለፊያ ከተማ በመሆኑ ከተማዋ ላይ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ከመንግስት ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ከመቸውም ጊዜ በላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስተያየታቸውን በተለይም የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በከተማዋ ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ባደረገው ቆይታ ነዋሪዎቹ አስረድቷል።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 28/03/14 E.C , Sodo, Ethiopia