በሽኝት ቦታ የተገኙ የኢፌዴሪ በመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር የቆላማ አከባቢ ምርምርና ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እንድርያስ ጌታ እንዳሉት ይቅርታን፣ ፍቅርንና መተማመንን የሚወድ ህዝብን በማገልገሌ ልገልጸው የማልችለው ደስታ በውስጤ ተሰምቶኛል ብለዋል።
በዞኑ አጠቃላይ ህዝብና አመራሩ ትጋትና ጥረት በፌደራልና በክልሉ ደረጃ ያሉ የዎላይታ ተወላጆች እንድሁም የፌደራልና የክልሉ መንግስት የሰጡት እገዛ የዎላይታ ገጽታን የተሻለ ማድረግ አስችሏል ብለዋል።
ህዝቡ የትኛውንም ጥያቄ በትግስትና በእርጋታ የሚጠይቅ መሆኑን ጠቅሰው ታጋሽነቱ እና ትዕግስቱ በዎላይታ ህዝብ ዘንድ ሰርጾ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል።
የህዝባችንና የኢትዮጵያን የብልጽግና ዕድገትን በጋራ ከቆምን፣ ከተባበርን፣ ከተጋገዝንና ከተደማመጥን አንዳች ነገር ሳይጎድል ማረጋገጥ እንችላለን ብለዋል።
ጠላት ወደ ውስጣችን ገብቶ እንዳይከፋፍለንና እንዳይለያየን አንድነታችንን ጠብቀን ህዝባችን የሚያነሳውን የትኛውንም ጥያቄ ደረጃ በደረጃ በተሟላ ሁኔታ በመመለስ መልካምና ምቹ ተግባር ማየት እንደሚቻል አመልክተዋል።
ዞኑን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲያገላገሉ የነበሩ አሁን የዎላይታን ብሎም የመላው የሀገራችንን ህዝብ ክብርና ውክልና ወስደው የተሾሙትንም መልካም ምኞታቸውን የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ገልጸዋል።
ህዝቡን በታማኝነትና በቅንነት ያገለገሉት አሁንም በተሰማሩት የስራ መስኮች በልበ ሙሉነት እንደሚያገለግሉ ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉ የዎላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ አስታውቀዋል ማለታቸውን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
