ጦርነቱ በተራዘመ ቁጥር በሀገር ኢኮኖሚ እየደረስ የሚገኘው ጉዳት ቀላል የማይበል በመሆኑ ዘላቂ ሠላም እንደሚያስፈልግ የዎላይታ ዞን ነዋሪዎች አሳሰቡ።
በድህረ ጦርነት ዝንፈቶችን ፈጥኖ ማረም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በወላይታ ዞን በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ነዋሪዎች ተወያይተው ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቋል፡፡
በሁሉም ወይይት መድረኮች የአከባቢን ሰላምን ለማስጠበቅ፣ የማህበራዊ ችግሮችና የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳይሞትና እንዳይነዳ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡም አስታውቀዋል፡፡
በህልውና ዘመቻ ወቅት የተገኘው የህዝባችን አንድነት ሳይሸራረፍ ተጠናከሮ እንዲቀጥልና ለሁለንተናዊ ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ እንተጋለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ጦርነቱ በተራዘመ ቁጥር በሀገር፣ በሕዝብና በኢኮኖሚ እያደረስ ያለው ጉዳት ቀላል የማይበል ስለሆነ ዘላቂ ሠላም እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡
በሁሉም አከባቢዎች ንጥቂያ፣ ዝርፍያ እና ሥርቆት እየበረከተ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸው አካባቢያቸውን ተደራጅተው ከወትሮ ሳይዘናጉ ነቅተው እንደሚጠበቁም አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን ለአገራቸው ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጡና ፈጽሞ የማይደራደሩ መሆናቸውን በተግባር ማሳየታቸውንም አድንቀዋል፡፡
የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄችን በተቀናጀ መንገድ መፍታት እንዳለበት የጠየቁት ነዋሪዎቹ ዘላቂ ድልና ለውጥ ለማምጣት አንድነታችን ይበልጥ መጠናከር አለበት ብለዋል፡፡
ሠላም አሻፈረኝ፣ አያስፈልግም፣ አልፈልግም በማለት ሀገራችንን ለማፍረስና ለመበታተን አቅደውና አልመው በሚሠራው በማንኛውም አካል ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ መወሰድ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ሉዓላዊነታችንን አስጠብቀንና ጠላቶቻችንም ደግመው ለጦርነት እንዳያስገቡን እያደረግን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያን ሰላምና ዴሞክራሲ የሚተክሉና የሚያጸኑ ስራዎችን መስራት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በየደረጃው የተካሄዱ ውይይቶች መልካም እድሎች የፈጠረ ሲሆን ቀጣይ በሀገራዊ አንድነትና ትብብር ላይ የላቀ ጠቀሜታ እንዳለውም መገለፁን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
