በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት አምስት ሰዎች በዋስ እንዲለቀቁ ፍርድቤቱ ትዕዛዝ መስጠታቸው ተገልጿል።

በቀድሞ የዎላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች እና በደቡብ ክልል ባለው ፍርድ ሂደት በዛሬው ቀን በተካሄደው ችሎት በጉዳዩ ከተጠረጠሩ 15 ሰዎች መካከል አምስት ሰዎች በዋስ እንዲለቁቁ ትዕዛዝ መሰጠቱን ከጠበቃቸው ተመስገን ዋጃና WT አረጋግጧል።

ቀጣይ የቀሪዎቹ የፍርድ ሂደት ለ30/02/2013 ዓ ም ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ዛሬ በዋስ እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው መካከል

1 ጎበዜ አበራ የዎብን ህዝብ ግንኘነት
2 እህተነሽ ኤሊያስ የቀድሞ አመራርና የዩንቨርስቲ መምህርት
3 መብራቱ ጳውሎስ የዞን ገቢዮች
4 ተስፋዬ አበበ- የዎልማ ጠበቃ
5 አክሊሉ ደስታ ከንግድ ማህበራት ይገኙበታል።