በዎላይታ (Gibe-3) በኡማ ኤለክትሪክ ማመንጫ ግድብ በተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ በቀን እስከ 5 ቶን አሳ እየወጣ ነው

በግቤ 3 ኤለክትሪክ ማመንጫ ግድብ መገደቡን ተከትሎ በዎላይታ ዞን በሶስት ወረዳዎች በተላይም በክንዶ ኮይሻ ወረዳ በተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሀይቅ ላይ አንድ የሆላንድ ኩባንያ በአሳ ማምረት ስራ ተሰማርቶ በቀን እስከ 50 ኩንታል ወይንም 5 ቶን አሳ እየወጣ እንደሚገኝ WT በቦታው ተገኝቶ አረጋግጧል።

ኩባንያው የአሳ ምርቱን በቦታው ማቀነባበሪያ ማሽን በመትከል ምርቱን ለአለም አቀፉ ገበያ ጥራትን የጠበቀውን ለማቅረብ አልሞ እየሰራ እንደሚገኝ ያገኘነው ያመለክታል።

ቢሆንም ኩባንያው በአሁኑ ወቀት የሚያመርተውን አሳ ምርት የሚመለከታቸው አካላት ክትትልና ድጋፍ ባለመኖሩ ለሀገር ውስጥ ገበያ ብቻ ለማቅረብ እንደተገደደም  ለWT ገልጿል።

የአሳ ማቀነባበሪያ ማሽኖች ከውጭ ሀገር በውድ ዋጋ ተገዝቶ ቢመጣም ማሽኑ ስራ ላይ እንዲገባ የኤለክትሪክ ሀይል አቅርቦት ባለመኖሩ እቃዎቹ ተቀምጧል።

ኩባኒያው የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላትን የኤለክትሪክ አገልግሎት እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም እስካሁን ምንም ምላሽ አልሰጠም ሲል አንድ የኩባንያው ሰራተኛ ለWT ቅሬታ አቅርቧል።

በአሁኑ ወቅት በሙሉ አቅም የተመረጡ የአሳ ዝርያዎችን በሙሉ አቅም በማምረት ለአከባቢው ተወላጆች ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት እንቅፋት እየገጠመው ቢሆንም #ጀነሬተር በመጠቀም ለተወሰኑ ስራ አጥ ወገኖች የስራ ዕድል በመፍጠር ለሀገር ውስጥ ገበያ የአሳ ምርት እያቀረቡ እንደሆነም ተነግሯል።

የኡማ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ(#Gibe-3) መገደቡን ተከትሎ በተፈጠረው በዚሁ ሀይቅ የአሳ ምርት ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ ሆቴሎች እና ሎጆቸን ለመስራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች አከባቢው ምቹ መሆኑን WT Media and Advertising Service በቦታው በተገኘበት ወቅት አረጋግጧል።

በመሆኑም የኤሌክትሪክ ሀይል(#Gibe-3) በቅርበት ከ1887 በላይ ሜጋ ዋት የሚያመነጭ ግድብ እያለ ባለሀብቶች የኤሌክትሪክ ሀይል አጥቶ ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ የሚያደርግ ስለሆነ የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጡ እያልን አከባቢውን ለተለያዩ አገልግሎት ለማልማት የሚፈልግ ድርጅት ሆነ ግለሰብ ካለም ያልተነካ ሀብት በመጠቀም ዕድሉን እንዲጠቀም በዚሁ አጋጣሚ ልንገልጽ እንወዳለን።

ቀጣይ ኩባንያው ለWT ያቀረበው ቅሬታ የደረሰበትን ተከታትለን እናቀርባለን።

https://wolaitatimes.com.et/?p=187