የቀድሞ የሊቃ ትምህርት ቤት ተማሪ የነበረው በረከት ይስሐቅ ከደቡብ ኮሪያ ተክኖሎጂ ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ ተመረቀ

በጊዜው በኢትዮጵያ (2007ዓ.ም) የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከተፈተኑት ከፍተኛ ውጤት (646) በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁለተኛ የወጣው የቀድሞ ሊቃ ተማሪ የነበረው በረከት ይስሐቅ በስኮላርሽፕ ውድድር አልፎ ከአንጋፋው ደቡብ ኮሪያ ተክኖሎጂ ተቋም KAIST (Korean Advanced Technology Institute) በኤለክትሮ መካኒካል እንጂኔሪንግ ትምህርት ዘርፍ ተምሮ በከፍተኛ ማዕረግ መመረቁን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በየአመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ባለብሩ አዕምሮ ልጆችን በከፍተኛ ውጤት እያመረተ ከሀገሪቱ ዩንቨርስቲዎች ባሻገር በተለያዩ እውቅ አለምአቀፍ ዩንቨርሲቲዎች እንዲቀላቀሉ በማድረግ በሀገሪቱ ሰው ሀብት ልማት ላይ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ የሚገኝ በዎላይታ ልማት ማህበር ስር የሚተዳደር የህዝብ ትምህርት ቤት መሆኑ ይታወቃል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: