FB_IMG_1647433427983

ትናንትነው ዕለት በዎላይታ ዞን ከቦዲቲ ወደ ጋቼኖ ሲጓዝ በነበረው ሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ባጋጠመው ትራፊክ አደጋ የሰው ህይወት ማለፉ እና ከባድ ጉዳት መድረሱን ተገልጿል።

በወረዳው አደ ኮይሻ ትምህርት ቤት አከባቢ በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ 3 ከባድ ጉዳት እና 16 ቀላል ጉዳት መድረሱን የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት አስታውቋል።

አደጋው የደረሰው በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 12:00 ሰዓት ገደማ ሲሆን የአደጋው መንስኤ የፊት በቀኝ በኩል ያለው ጎማ በመፈንዳቱ አደጋዉ ልደርስ ችሏል።

ከባድና ቀላል አደጋ የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተገልጿል።

በተሽከርካሪ ምክንያት የሚደርስ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል ጉዞ ከመጀመርዎ በፊት የተሽከርካሪዎን ክፍሎች መፈተሽ እንደሚገባ በመረጃው ተመልክቷል።